Thursday, April 23, 2020

አብሽ

Fenugreek – Abish

Abish. This spice even has its own dish: minchet abish – ground beef pan fried with spices. We call it fenugreek in English, and it’s a staple of Indian curries.

አብሽ

አብሽ:: ይህ ቅመም ራሱን የቻለ የምግብ አይነትም ይሆናል: ምንቸት አብሽ – የተፈጨ ስጋ በቅባት በጋለ መጥበሻ ላይ በማድረግ በቅመም የተጠበሰ::

GINGER - Zinjibel

Ginger – Zinjibel

Lots of fresh ginger in many if not most Ethiopian dishes, along with garlic and onions, ginger is a big player.

Fresh ginger is used in many Ethiopian dishes.

ዝንጅብል

ብዙ አዲስ ያልከረሙ ዝንጅብሎች በአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ምግቦች ላይ፣ ከነጭ ሽንኩርት እና ከቀይ ሽንኩርት ጋር በመሆን ዝንጅብል አይነተኛ ምግበ ይሆናል::

አዲስ ዝንጅብል በአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ምግቦች ላይ እንጠቀመዋለን

AWAZE

Awaze

Awaze is a common chilli sauce blend made in many different ways. A basic or common version is nitre kibbeh, berbere, lemon, ginger or garlic and some form of alcohol, this could be Tej, Gin or even wine. This sauce is used as a side dip or to pur and to cook with, like Awaze Tibs.

አዋዜ

አዋዜ የተለመደ የቃሪያ ስልስ ቅይጥ ሲሆን በተለያየ መንገድ ይዘጋጃል:: መሰረታዊው እና የተለመደው አዘገጃጀቱ በንጥር ቅቤ፣ በበርበሬ፣ በሎሚ፣ በዝንጅብል ወይም በነጭ ሽንኩርት እና በተወሰነ መልኩ አልኮል ተጨምሮ ነው አልኮሉም ጠጅ፣ ጅን ወይም ወይን ሊሆን ይችላል:: ይህን ስልስ እያጠቀስን ወይም በምናዘጋጀው ምግብ ላይ እየነሰነስን መሆን አለበት፣ ልክ እንደ አዋዜ ጥብስ:

Mekelesha መከለሻ

Mekelesha or Kimen Wot is a blend of 7 spices – Korerima – Cloves – Cinnamon Sticks – Whole Black Pepper – Cumin – Nutmeg – Timiz / Indian Long Pepper

መከለሻ

መከለሻ ወይም ቅምን ወጥ የሰባት ቅመሞች ቅይጥ ነው እነዚህም : ኮረሪማ _ ቅርንፉድ _ ቀረፋ እንጨት _ ሙሉ ጥቁር በርበሬ _ አዝሙድ _ ቆንዶ በርበሬ _ ጥምዝ

KOSERET

Koseret or Lippia Javanica is a member of the verbena family. Now there about 200 strains of Lippia and i am for sure uncertain about all of them found outside of Ethiopia.

The Ethiopian variety has a light herbaceous taste and could be described as being close to Oregano but with a more pungent floral edge. Very similar in use as Besobela, in that it can be used as a dried herb to sprinkle on food or is great in a sauce. It is widely used with Ethiopian cooking and a must have for many dishes including Kibe (Ethiopian spiced butter).

ኮሰረት

ኮሰረት ወይም ሊፒአ ጃቫኒካ የባለአበባ እጽዋት ክፍል ነው:: ከ 200 በላይ የኮሰረት ዝርያወች ይገኛሉ ግን ሁሎችም ከኢትዮጵያ ውጭ ይገኛሉ በሚለው ሀሳብ ምንም ማረጋገጫ የለም::

የኢትዮጵያ አይነቱ ኮሰረት ቀላል ግንድ የለሽ ጣዕም ያለው ግን የሚገለጽበት መንገድ ጠንካራ የሆነ ሽታ እና ጣዕም ያለው ባለ አበባ ዕጽ አይነት ነው:: ከ በሶ ብላ ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው፣ በደረቅ መልኩ ምግብ ላይ በመነስነስ በሶስ ውስጥ የምንጠቀምበት ነው::  በአብዛኞቹ የኢትዮጵያን የማብሰል ሂደት ውስጥ በብዛት የምንጠቀምበት እና ለብዙወቹ አስፈላጊ የሆነ በቅቤም ውስጥ የምንጠቀመው ነው::

BESO

An incredibly delicate herb that is sun-dried and often ground to a powder. It has purple flower and a delightful smell. Also know as sacred basil, this herb is an absolute must for many Ethiopian dishes. Use it as you would a regular basil or oregano type of herb. Fantastic as a rub for BBQ meats, chicken or fish, super in a Ragu or tomato based sauce. Its uses within Ethiopian cooking is wide and can be found in Kibe (kibbbeh, qiibe) a Ethiopian spiced butter, Shiro, Berbere and many other dishes. Regular Basil found outside Ethiopian, meaning a Italian type of affair is no substitute.

በሶ ብላ

ይህ ድንቅ እጽ በጸሀይ በማድረቅ እና በአብዛኛው ተፈጭቶ የሚዘጋጅ ነው:: አበባው የወይን ጠጅ ቀለም እና ማራኪ ሽታ ያለው ነው:: ሳክርድ ባሲል ተብሎም ይታወቃል፣ ይህ እጽ ለአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ምግቦችም እንደ ግዴታ እንጠቀምበታለን:: እንደ ተለመደው ባሲል ወይም ኦርጋኖ እንደሚባሉት እጾች ልንጠቀመው እንችላለን:: ለባርባኪው ስጋ፣ ለዶሮ ወይም ለአሳ ብንጠቀመው አስደናቂ ውጤት ይሰጠናል በቲማቲም ስልስ ወይም በራጉ ደግሞ ልዩ ይሆናል:: በኢትዮጵያ ምግብ አዘገጃጀት ውስጥ ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ ነው በንጥር ቂቤ፣ በሽሮ፣ በበርበሬ እንዲሁም በሌሎች ምግቦች ውስጥም እናገኛዋለን:: በተለምዶ ባሲል የሚባለውን እጽ ከኢትዮጵያ ውጭ እናገኛዋለን፣ ማለት የጣልያን አይነቱ ጉዳይ ተቀያሪ ሊሆን አይችልም::

Korarima or Korerima

Korarima or Korerima

Many recipes we see online for Ethiopian cooking, state the use of cardamon. This is of course correct but the type of these pods differs enormously. In Ethiopian cuisine, the cardamom also known as Korarima, Korerima, False Cardamom and Ethiopian Cardamom, is hugely different in taste, smell and size to its smaller black and green cousins. The smaller black pod used in lots of Indian (Asian) cooking does has a small resemblance and is far closer is taste than the green type. Known as Hill cardamom, Bengal cardamom, greater cardamom, Indian cardamom, Nepal cardamom, winged cardamom, or even brown cardamom, is roughly a eighth of the size as the one used in Ethiopia. The more common green cardamom is much smaller than even its black cousin and in taste, does not even get close to much larger Ethiopian variety. Aframomum corrorima or what we call Korerima is used in many ways in Ethiopian cuisine including Berbere, Mitmita, Nite Kibbeh or Niter Kibe (Spiced butter) as well on occasions in coffee and as a herbal medicine. The importance of Korerima cannot be over stated within Ethiopian Cooking. The bottom line is, when cooking any Ethiopian food, stay away from the green Cardamom, maybe if you just cannot get Korerima use the smaller black Cardamom, but of course if you can get the real deal and make your Ethiopian food taste as it should.

ኮረሪማ

አብዛኞቹ የድረገጽ የኢትዮጵያ ምግብ ማብሰል መምሪያዎች፣ አጠቃለው ኮረሪማ ብለው ይናገራሉ:: በሀሳብ ደረጃ ትክክል ናቸው ግን የፍልፋዩ ነገር እጅግ በጣም ይለያያል፣ ይህም ኮረሪማም ኮረሪማ ተብሎ ቢታወቅም፣ የውሸት ኮረሪማና የኢትዮጵያ ኮረሪማ፣ በብዙ ነገር ይለያያሉ በ ጣዕም፣ በሽታ እና በመጠን ከ ትንሹ ጥቁሩ እና አረንጓዴው አይነቱ ይለያል:: ትንሹና ጥቁሩ ፍልፋይ በአብዛኞቹ የህንድ የማብሰል ሂደት ውስጥ ይጠቀሙታል በትንሹም መመሳሰል አለው በጣዕም ደረጃ ግን ከ አረንጓዴው አይነቱ ምንም መመሳሰል የለውም:: በሌሎች አጠራሮቹም ሂል ኮረሪማ፣ ቤንጋል ኮረሪማ፣ ታላቁ ኮረሪማ፣ የህንድ ኮረሪማ፣ የኔፓል ኮረሪማ፣ ክንፋሙ ኮረሪማ ወይም ቡናማ ኮረሪማ እንኳ በመጠን ደረጃ የኢትዮጵያን ኮረሪማ አንድ ስምንተኛ ነው የሚሆነው:: በብዛት የተለመደው አረንጓዴው ኮረሪማ እንኳ በመጠን ከጥቁሩ ኮረሪማ በጣም ያነሰ ነው በጣዕሙም ቢሆን በጣም ትልቅ ከሆነው የኢትዮጵያ አይነቱ ጋር ምንም መቀራረብ የላቸውም:: አፍራሞሙም ኮረሪማ ወይም እንዲሁ ኮረሪማ ብለን የምንጠራው በኢትዮጵያውያን የምግብ አዘገጃጀት በተለያየ መልኩ ይጠቀሙታል ከነዚህም ውስጥ በበርበሬ፣ በሚጥሚጣ፣ በንጥር ቅቤ እንዲሁም እነደሁኔታው በቡና እና በ እጽዋት መድሀኒት ያገልግላል:: በኢትዮጵያውያን የማብሰል ሂደት ውስጥ የኮረሪማ ጥቅም ሊጋነን አይችልም:: ሊሰመርበት የሚገባው፣ የኢትዮጵያን ምግብ ስታዘጋጁ አረንጓዴ ኮረሪማ ፈጽሞ መጠቀም አያስፈልግም፣ ምናልባት እንኳ ትክክለኛውን ኮረሪማ ካላገኛችሁ ትንሽየዋን ጥቁሯን ኮረሪማ ይጠቀሙ፣ ግን አወ ትክክለኛውን ነገር ማግኘት ካልቻላችሁ የምትሰሩት የኢትዮጵያ ምግብ ጣዕሙ ኢትዮጵያዊ መምሰል እንዳለበት መርሳት የለባችሁም::

Mitin Shiro

Shiro is a homogeneous stew whose primary ingredient is powdered chickpeas or broad bean meal. (Shimbra) It is often prepared with the addition of minced onions, garlic and, depending upon regional variation, ground ginger or chopped tomatoes and chili-peppers. Shiro is served atop injera or kitcha (a sugarless pancake kind of bread). However, it can be cooked in shredded taita and eaten with a spoon, this version would be called shiro fit-fit. Shiro is an essential part of Ethiopian. It is a favorite dish during special occasions, including Lent, Ramadan, and other fasting seasons. It is a Vegan food, but there are variations including Nitre Kibbe (a spiced, clarified butter) or meat (in which case it is called bozena shiro). Mitten Shiro is a blend of shiro powder and pre mix spices.

ምጥን ሽሮ

ሽሮ  ወጥ በመሰረታዊነት የሚዘጋጀው ከተፈጨ ሽንብራ ወይም ከ አተር የሚቀመም አንድ አይነት የሆነ ወጥ ነው:: (ሽንብራ) በአብዛኛው ሲዘጋጅ ሽንኩርት ተከትፎ፣ ነጭ ሽንኩርት እና፣ የአካባቢውን ልዩነት መሰረት ባደረገ መልኩ ደግሞ፣ የተፈጨ ዝንጅብል ወይም የተከተፈ ቲማቲም እና የቃሪያ ማጣፈጫ:: ሽሮ የሚቀርበው በእንጀራ ላይ ወይም በቂጣ(ስኳር የሌለበት የፓንኬክ ዳቦ የሚመስል) ተደርጎ ነው:: ነገር ግን፣ በፍትፍት መልኩ አዘጋጅቶ በማንኪያ መመገብ ይቻላል፣ ይህኛው አይነት ሽሮ ፍትፍት ይባላል:: ሽሮ የኢትዮጵያውያን ዋና የሆነ ነገር ነው:: በተለዩ ሁኔታወች ላይም ተወዳጅ ምግባቸው ነው ተወዳጅነቱም፣ በሁዳዴ ጾም፣ በረመዳን እንዲሁም ሌሌች የጾም ወቅቶችን ያካትታል:: የአትክልት ተመጋቢወች ምግብ ቢሆንም ንጥር ቅቤ ወይም ስጋ ተጨምሮበት በቦዘና ሽሮ መልኩ ሊዘጋጅ ይችላል:: ምጥን ሽሮ የሽሮ ዱቄት እና ቀድመው ከተዘጋጁ ቅመሞች የሚቀየጥ ነው::

Mitmita

If Berebere is the “Big Daddy” of Ethiopian spices then Mitmita would be classed as the “Heavyweight”.

This amazing blend packs a real punch on the heat seekers chart for sure. Like Berbere, Mitmaita is often made at home and the blends can change from house to house.

Mitmita (Amharic: ሚጥሚጣ?, IPA: [mitʼmitʼa]) is a powdered seasoning mix used in Ethiopian cuisine. It is orange-red in color and contains ground African birdseye chili peppers, cardamom seed, cloves and salt. It occasionally has other spices, including, but not limited to, cinnamon, cumin and ginger. The mixture is used to season the raw beef dish. In addition, mitmita may be presented as a condiment and sprinkled on other foods.

ሚጥሚጣ

በርበሬ የኢትዮጵያ ቅመማት “ትልቁ አባት” ከሆነ ሚጥሚጣ ደግሞ “ባለከባድ ሚዛን” ከሚለው ይመደባል::

ይህ አስገራሚ ቅይጥ የሚያቃጥል ነገር ለሚፈልጉ ጥሩ በርግጥም ተመራጩ ነው:: ልክ እንደ በርበሬ፣ ሚጥሚጣም የሚዘጋጀው ቤት ውስጥ ነው እንደየቤቱም  ሊለያይ ይችላል::

ሚጥሚጣ በኢትዮጵያ ምግብ ውስጥ ለማጣፈጫነት የሚጠቀሙበት የተፈጨ ቅልቅል ነው:: ቀለሙ ብርቱካናማ ቀይ ሲሆን በውስጡ የያዛቸው የአፍሪካን ወፍስየ ቃሪያ ማጣፈጫ፣ ኮረሪማ ፍሬ፣ ቅርንፉድ እና ጨው ነው:: እንደየሁኔታው የሚጨመሩ ቅመሞችም ቀረፋ፣ አዝሙድ፣ እና ዝንጅብልን ያካትታል ግን እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም:: ይህ ድብልቅ ለቁርጥ ስጋ ማጣፈጫነት ያገለግላል:: ከዚህ በተጨማሪም፣ ሚጥሚጣ በሚቀርበው ምግብ ላይ እየተነሰነሰ በማጣፈጥ እንጠቀመዋለን::

Niter Kibbeh

Niter Kibbeh

Niter Kibbeh (Nit’ir Qibe) is a spiced clarified butter, something like India’s ghee, but flavoured with spices.

Again this can change from house to house. It is a richly spice butter that adds a super taste to many Ethiopian dishes.

Please see our video for one of our versions:

ንጥር ቅቤ

ንትር ቅቤ) በቅመም የተጣራ ቅቤ ነው፣ ልክ እንደህንዳውያኑ ጊህ፣ ግን ይህ በቅመም የተጣፈጠ ነው::

ይህም ደግሞ እንደየቤቱ ሊለያይ ይችላል:: በብዛት ቅመም የገባበትና ለኢትዮጵያ ምግቦች ልዮ ጣዕምና የሚሰጥ ነው

Berbere

You will not get very far in your Ethiopian cooking without this mainstay blend. This we could say is the “Big Daddy” of Ethiopian cuisine. With a deep red paprika colour, berbere is a blend of many spices with its base very much set in the red chilli corner.

It is often made at home in Ethiopia and thus everyone makes it their own style and of course see theirs as the supreme version. The process is a lengthy one, starting off with the large red chilli (Also called Berbere by the way) being dried and then crushed. Then a combination of onion, garlic, ginger, fenugreek, black cardamon, cumin, nutmeg and even cinnamon are added and the complete mixture is then ground to a fine powder. Of course “Mums” version is always the best.

Berbere is usually made with fresh onion, garlic and ginger, but you can of course use dried powders, although not the same. But give it a go and have fun. If you want the real deal, we would suggest that you buy some, preferably direct from a source in Ethiopia. A few notes on herbs & spices in Ethiopian Berbere. Cumin. This is not the same as regular cumin you get in stores outside of Ethiopia. In fact it is nothing like it and has no features in look, smell or taste. ጥቁር አዝሙድ or Tikur Azmud. In English it is commonly referred to as Black Cumin or Black Caraway, although it has no relation to the common Cumin or Caraway that is used as a spice in cooking. It is also known as Black Seed (Nigella Sativa). Black Cardamon. Again these are very different from the Indian types found outside of Ethiopia. They are much much bigger and contain, many small seeds that have a eucalyptus aroma. Korerima or Korarima (Aframomum corrorima) are a vital part of Ethiopian cooking and although you can find the smaller black cardamon that are sometimes use in Indian cooking, they do not contain the same punch. Using green cardamon will result in a 100% failure in your berbere, these are so different, there is is just no point trying them. So the bottom line is, Ethiopian Berbere is fairly hard to make properly, even if you have all the correct ingredients. Now do not let this stop you having a go and creating your own, but if you need that authentic Ethiopian, it will take a lot of practice and as we have found, Mums version beats ours overtime. You can find many Recipes on our site on both the Recipes Pages and the Video Section. Please let us know how you got on!

በርበሬ

ይህን የኢትዮጵያ የምግብ አዘገጃጀት ዋና የሆነውን ሳይጠቀሙ በማብሰል ብቃትዎ ለመዝለቅ አይችሉም። ይህን ቅመም የኢትዮጵያ ምግብ “ትልቁ አባት” ብለን ልንሰይመው እንችላለን። ባለ ጥልቅ ቀይ ቀለሙ በርበሬ የተለያዩ አይነት ቅመሞች ውጤት ቢሆንም ዋነኛ መሰረቱ ዛላ በርበሬ ነው

አብዛኛውን ጊዜ በተለምዶ ቤት ውስጥ የሚሰራና እያንዳንዱ የራሱ በሆነ ዜዴ የሚያዘጋጀው ስለሆነ ሁሉም የየራሱን ከሁሉም የበለጠ እንደሆነ ያምናሉ:: ሂደቱም ጊዜ የሚወስድ ነው ፣ የሚጀምረው ከትልቁ ቀይ ቃሪያ (በነገራችን ላይ ዛላ በርበሬ ይባላል) ከደረቀ በኋላ ይከሰከሳል:: በመቀጠልም ከሽንኩርት ፣ ከነጭ ሽንኩርት ፣ ከዝንጅብል ፣ አብሽ፣ ኮረሪማ ፣ ጥቁር አዝሙድ ፣ ከሙን ፣ ቆንዶ በርበሬ እና ቀረፋ ሳይቀር ከተዋሀደ በኋላ የተሟላው ድብልቅ ጥሩ ሆኖ ይፈጫል:: አወ ልክ ነው “የእናቶች” የሙያ ውጤት ሁልጊዜ አሪፍ ነው::

በተለምዶ በርበሬ የሚዘጋጀው ከአዲስ ሽንኩርት ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ዝንጅብል ነው ፣ ነገር ግን እንዳስፈለጊነቱ በደረቅ ዱቄት መልክ መጠቀም ይቻላል:: ምንም እንኳ ተመሳሳይ ባይሆንም:: ነገር ግን ይሞክሩት እና ይደሰቱ:: እውነተኛውን ነገር ከፈለጉ ግን ፣ በቀጥታ እንድትገዙ እንመክራለን ፣ ማለትም ቀጥታ ከኢትዮጵያ ምርቶች:: የተወሰኑ ማስተዋሻወች በ ኢትዮጵያ ቅጠላ ቅጠል እና የበርበሬ ቅመሞች:: ከሙን፦ ይህ ከሙን ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉ ሱቆች እንደምታገኟቸው ሌኮች ከሙኖች አይደለም:: በርግጥ እንደውም በሽታም ሆነ በጣዕሙ እንዲሁም በይዘቱ ምንም የሚያመሳስል ነገር የላቸውም::

ጥቁር አዝሙድ፦ በእንግሊዘኛው የተለመደው አጠራር ብላክ ከሙን ወይም ብላክ ካራዋይ ነው ፣ ምንም እንኳ ለማብሰል ከተለመደው ከሙን ወይም ካራዋይ ቅመም ጋር ግንኙነት የለውም:: ጥቁር ዘር(ኒጌላ ሳቲቫ) በመባልም ይታወቃል:: ብላክ ካርዳሙን፣ ይህም ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኘው የህንድ አይነቱ የተለየ ነው

እነዚህኞቹ በጣም በጣም ትልቅና በውስጣቸው ብዙ ትንንሽ ዘሮችን የሚይዙ ልክ እንደ ኢካላፕተስ ዛፍ ሽታቸው ያማረ ነው:: ኮረሪማ (አፍራሞሙም ኮሮሪማ) በኢትቶጵያ የምግብ አዘገጃጀት ውስጥ በጣም ጠቃሚው ነው እና ቢሆንም አንዳንዴ በህንዳዊያን የምግብ አዘገጃጀት እንደሚጠቀሙት ትንንሽ ኮረሪማወችን ልታገኙ ትችላላችሁ ያን ያህል ግን ቃና የላቸውም:: ለበርበሬ አዘገጃጀት አረንጓዴ ኮረሪማ መጠቀም 100% ስህተት ነው፣ ይህ በጣም የተለየነው፣ እንደዛ መሞከር ትርጉም የለሽ ልፋት ነው::

ስለዚህ ሊሰመርበት የሚገባው ነገር፣ ትክክለኛ ቅመም ቢኖርም እንኳ የኢትዮጵያን በርበሬ በአግባቡ ለማዘጋጀት ትንሽ አስቸጋሪ ነው:: ይህ ማለት ግን የራሳችሁን ሙከራ አታድርጉ ማለት አይደለም፣ ግን ጥሩ የሆነ ኢትዮጵያዊ ከፈለጋችሁ፣ እንደገኘነው ብዙ ልምምድ የሚያስፈልገው ነው፣ የእናቶች ልዩ አይነት ስራ የኛን በጊዜ ሂደት ይበልጠዋል:: በድረገጻችን በ ምግብ አዘገጃጀት መምሪያ ገጽ እና በቪዲዮ ክፍሎች የተለያዩ የምግብ አዘገጃጀት መምሪያ ታገኛላችሁ:: እንዴት እንዳገኛችሁት እባካችሁ አስታውቁን

Quick Guide to Every Herb and Spice in the Kitchen – በማድቤት ውስጥ የእያንንዱ ቅጠል እና ቅመም ፈጣን መመርያ

ደረቅ ቅጠሎች እና ቅመሞች አሳፎቲዳ (አሳፌቲዳ) – አሳፎቲዳ በህንድ አመጋገብ ውስጥ የምግብ መፈጨትን ለመርዳት የሚጠቅም ሲሆን የበሰለ ዝንጅብል ሽንኩርት ቃና ያለው ጠንካራ ሽታ አለው፡፡ አቾቴ ማጣበቂያ እና ዱቄት ...