Friday, April 10, 2020

ኣክሱምና ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን

ኣንዳንድ የአክሱም ነገስታት የአማርኛ ስም ነበራቸው ፤ ኣማርኛ ቋንቋም የሚስጥር ቋንቋ ኣድርገው ይጠቀሙ ስለነበር ኣክሱም የኣማራ ኣገር ነበር” ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን
==========================================================
“ኣንዳንድ የአክሱም ነገስታት የአማርኛ ስም ነበራቸው ፤ ኣማርኛ ቋንቋም የሚስጥር ቋንቋ ኣድርገው ይጠቀሙ ስለነበር ኣክሱም የኣማራ ኣገር ነበር” ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ኣረጋው ፤ የኣፄ ዮሃንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ በሚለው ጽሁፉ ላይ ኣስፍሮታል።
(በ EthioReport ላይ May 4, 2017 ፖስት ኣድርጌው ነበር ፡ በ http://ethioreport.com/blog/2017/05/04/  ማግኘት ትችላላችሁ)
ለእንዲህ ኣይነቱ የሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ኣረጋው ኣነጋገር ነበር የIBM programmer እና instructor የሆነው ጆርጅ ፉችሰል Garbage In, Garbage Out (GIGO) ብሎ የጠራው። “Garbage In, Gospel Out,” ያለው።
ይህም ማለት “ነገርን ሳያዳምጡ ፡ እህልን ሳያላምጡ” እንደሚባለው የኣማርኛ ምሳሌኣዊ ኣነጋገር ነው።
Yemane Abadi Gidey #Mekelle
”ታሪክን መማር ለሁሉ ሰው ይበጃል፤ የታሪክ ትምህርት ግን የሚጠቅም የእውነተኛ ታሪክ ትምህርት ሲሆን ነው ፤ እውነተኛውን ታሪክ ለመጻፍም ቀላል ነገር ኣይደለም፤ የኣገራችን ታሪክ ፀሓፊዎች ግን በነዚህ ላይ ኃጢኣት ይሰራሉ፤ በትልቁ ነገር ፈንታ ትንሹን ይመለከታሉ፤ በእውነት መፍረድንም ትተው በኣድልዎ ልባቸውን ያጠብባሉ፤” (ገብረሕይወት ባይከዳኝ፣ ኣጤ ምኒልክና ኢትዮጵያ)
“በነገስታቱ መጠሪያ የኣማርኛ ስም የሆነው የቱ / እንዴት ያለ ነው? ነገስታቱ የኣማርኛ ቋንቋ የሚስጥር ቋንቋ ኣድርገው ይጠቀሙ ከነበርስ ኣክሱም የኣማራ ኣገር ነበር ለማለት ያስችላል? የኣማርኛ ቋንቋ የሚስጥር ቋንቋ ኣድርገው ይጠቀሙ የነበሩ የኣክሱም ነገስታት እነማናቸው? የትኛውና መቼ ነበር ኣማርኛ ተናጋሪው ነው የኣክሱም ንጉስ ሆኖ ኣማርኛን ሲናገር የነበረው? ይህ ከሆነ እንኪያስ ኣሁን ከኣክሱም ውጭ ያለው (ከትግራይ ውጭ/በኣማራ ክልል) ያለው የኣሁኑ የኣማራ ህዝብ ለምን ትግርኛ መናገር ኣይችልም? መቸም ትግርኛው እቃ ሆኖ እዛው ጥለውት ወዳሁኑ የኣማራ ክልል ኣይሰደዱም። ወይም ኣሁን በኣክሱም/በትግራይ ክልል/ ያለው የትግራይ ህዝብ ለምን ኣማርኛ ቋንቋን መናገር ኣይችልም? ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ኣረጋው እንደሚለው የትግራይ ህዝብ ከየመን የኣማራ ህዝብን ለማገልገል የመጣ ከነበረለምን ጥንትም ኣሁንም ዓረብኛ ቋንቋን ኣቀላጥፎ መናገር ልቻለም/ኣይችልም? ቋንቋውን እዛው ጥሎት መጥቷል እንዳትለኝ ፤ ምክንያቱም ኣንዲት ለ5 ዓመት ሸቅል ወደዓረብ ሃገር የሄደች ኢትዮጵያዊትም እዛው ዓረብ ሃገር የለመደቺውን የዓረብኛ ቋንቋ እንደ ፒጃማ ኣውልቃ ኣትመጣም” የሚሉትን ጥያቄዎች ማየቱ ሓተታችን ለሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ኣረጋውም ለኣንባቢያንም ግልፅ ይሆናል።
1= ከኣክሱም ነገስታት ስም ዝርዝር ውስጥ የኣማርኛ ስም ያለው ንጉስ የለም።ንግስተ ሳባን ጨምሮ የኣክሱም ነገስታት ስም ዝርዝር እንይ፦
1) ንጉስ ቀዳማዊ ሚኒሊክ ፤
2) ንጉስ ዞስካለስ ፤
3) ንጉስ ተክሎምብሮተስ ፤
4) ንጉስ ኢንዱቢስ ፤
5) ንጉስ ኣፊላስ ፤
6) ንጉስ ዋዜባ ፤
7) ንጉስ ኦሳናስ ፤
8) ንጉስ ኢዛና ፤
9) ንጉስ ሳይዛና ፤
10) ንጉስ ኦኣዜባስ ፤
11) ንጉስ ኢዮን ፤
12) ንጉስ ኢባና ፤
13) ንጉስ ነዞል ፤
14) ንጉስ ኡሳስ ፤
15) ንጉስ ካሌብ ፤
16) ንጉስ ኣላሚዳስ ፤
17) ንጉስ ዋዜና ፤
18) ንጉስ ዋዜብ ፤
19) ንጉስ ልኡል ፤
20) ንጉስ ሓታዝ ፤
21) ንጉስ ሰይፉ ፤
22) ንጉስ እስራኤል ፤
23) ንጉስ ጌርሰም 1ኛ ፤
24) ንጉስ ጻሕማ ፤
25) ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ፤
26) ንጉስ ወሰን ሰገድ ፤
27) ንጉስ ፍረሰናይ ፤
28) ንጉስ ኣድረኣዛር ፤
29) ንጉስ ኣክላ ወድም ፤
30) ንጉስ ግርማ ሰፈር፤
31) ንጉስ ዘርጋዝ ፤
32) ንጉስ ደጌና ሚካኤል፤
33) ንጉስ ባሕሪ ኢክላእ ፤
34) ንጉስ ጉም ፤
35) ንጉስ ኣስጎጉም ፤
36) ንጉስ ለተም ፤
37) ንጉስ ተላተም ፤
38) ንጉስ ዖዳ ጎሽ ፤
39) ንጉስ ኣይዙር ፤
40) ንጉስ ደደም ፤
41) ንጉስ ወደደም ፤
42) ንጉስ ወደም ኣስፋረ ፤
43) ንጉስ ኢዛና 2 ኛ ፤
44) ንጉስ ኢላ ኣብርሃ ፤
45) ንጉስ ኢላ ኣስፍሃ ፤
46) ንጉስ ኢላ ሳሄል ፤
47) ንጉስ ኣጋቤ ፤
48) ንጉስ ኣላሚዳ 4 ኛ ፤
49) ንጉስ ያዕቆብ 1 ኛ ፤
50) ንጉስ ዳዊት፤
51) ንጉስ ኣርማህ 2 ኛ ፤
52) ንጉስ ዚታና ፤
53) ንጉስ ያዕቆብ 2 ኛ፤
54) ንጉስ ቤተ እስራኤል ፤
55) ንጉስ ኣናኢብ ፤
56) ንጉስ ኣላሚሪስ ፤
57) ንጉስ ጆኢል፤
58) ንጉስ ጌርሰም 2 ኛ ፤
59) ንጉስ ኢላ ገበዝ ፤
60) ንጉስ ኢላ ጻሓም ፤
61) ንጉስ ኢያትሊያ ፤
62) ንጉስ ሃታዝ 1 ኛ ፤
63) ንጉስ ሃታዝ 2 ኛ ፤
64) ንጉስ ኣርማህ 1 ኛ፤
65) ንጉስ ዘርኣ ያዕቆብ 1ኛ፤
66) መስፍን ባሕረ ነጋሽ ፤
67) ንጉስ ደጌና ደገን ፤
68) ንጉስ ኣምበሳ ውድም ፤
69) ንጉስ ድል ናዖድ ፤
70) ንጉስ ገብረ መስቀል ፤
71) ንጉስ ሮምሃይ ፤
72) ንጉስ ባዜን ፤ . . .
ራእሲ (ራስ) ሚካኤል ስሑል ፤ ንጉስ ቴዎድሮስ ፤ ንጉስ ዮሃንስ ፤ ልዑል መንገሻ ፤ ራእሲ(ራስ) ኣሉላ ኣባ ነጋ . . . እና ሌሎችም . . .”
ከነዚህ ውስጥ ከኣክሱም ነገስታት ስም ዝርዝር ውስጥ የኣማርኛ ስም ያለው ንጉስ የለም። በነገራችን ላይ "ኣፄ" የሚለው ቃል በኣማርኛ ትርጉም የለውም። ይህ ቃል "ሃፀየ" ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ወደ ትግርኛ ሲመለስ "ሓፀየ/ሓሰበ/ፈተወ" የሚለው ትርጉም ይሰጣል። ይህም የኣገርን ባል ሆኖ እንደ ሚስት ኣገርን መውደድ ያመለክታል። ለምሳሌ ሃፀይ ዮሃንስ ጣልያኖችን ለመውጋት ሲነሱ በነጋሪት ያሳወጁት ኣዋጅ የሚከተለውን ነበር ፦
“የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ፣ ልብ ኣድርገህ ተመልከት ኢትዮጵያ የተባለችው ኣንደኛ እናትህ ናት ፤ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፤ ሦስተኛ ሚስትህ ናት ፤ ኣራተኛም ልጅህ ናት። ኣምስተኛም መቃብርህ ናት። እንግዲህ ፣ የእናት ፍቅር ፣ የዘውድ ክብር ፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባድነት ፣ እንደዚህ መሆኑን ኣውቀህ ተነሣ።” ብለው ኣውጀዋል። ሃፀይ ዮሃንስ <<የኢትዮጵያ ባል>> ተብለውም ይታወቃሉ ፤ ለዚህም "ኢትዮጵያ ሚስትህ ናት" ኣሉ። እንግዲህ "ሃፀየ" ከሚለው የግእዝ ቃል ወደ ትግርኛ ሲመለስ "ሓፀየ/ሓሰበ/ፈተወ" የሚለው ትርጉም እሳቸውን ይገልፃል ማለት ነው ። ይሁን እንጂ "ሓፀየ" የሚለው ቃል ከጊዜ ብዛት " ሃፀይ" ወደሚለው ተቀይሯል።
2= ኣንዳንድ የኣክሱም ነገስታቱ የኣማርኛ ቋንቋ የሚስጥር ቋንቋ ኣድርገው ይጠቀሙ ከነበርስ ኣክሱም የኣማራ ኣገር ነበር ለማለት ያስችላል ወይ? ምክንያቱም እንደ ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ኣነጋገር "ኣንዳንድ የኣክሱም ነገስታት" በማለት ሓሳቡን ስለሚጀምር ኣብዛኞቹ ሳይሆኑ ጥቂቶቹ ብቻ የኣክሱም ነገስታቱ ናቸው የኣማርኛ ቋንቋን በሚስጥር ሲናገሩ የነበሩት ማለት ነው። ይህም ይሁን ከተባለ እንኳ መላው ኣገሩን (ኣክሱምን) ከነስልጣኔዋ የሚወክሉት ኣንዳንድ (ጥቂት) የኣክሱም ነገስታት ሳይሆኑ ብዙዎቹ የኣክሱም ነገስታትና ሰፊው የኣክሱም ህዝብ ነው ፤ ስለሆነም የኣማርኛ ቋንቋ መነገር የነበረበት በብዙዎቹ ኣክሱማውያን እንጂ በጥቂቶቹ (በኣንዳንዶቹ) ብቻ መሆን የለበትም። ምክንያቱም ኣገር ማለት ኣንዳንድ (ጥቂት) የኣክሱም ነገስታት ሳይሆኑ ሰፊው ኣክሱማዊው ህዝብ ስለሆነ። ባጭሩ ኣማርኛ የጥቂት የኣክሱም ነገስታት የሚስጥር ቋንቋ ከነበረ በሌላ ኣነጋገር የኣካባቢው (የሰፊው ህዝብ) ዋና የስራ ቋንቋ ትግርኛ ነበር ማለት ነው ፤ በዚህም ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ሳያስበው የኣክሱማውያን ዋና ቋንቋ (የሰፊው ህዝብ) ቋንቋ ትግርኛ እንደነበር እያረጋገጠልን ነው 😂
የኣማርኛ ቋንቋ ከትግርኛ የወሰዳቸው ቃላት ከ40% በላይ መሆኑን በረካታ ሙሁራን በመሰከሩበት ሁኔታ ኣማርኛን ከትግርኛ ለማስቀደም መቋመት ጋሪ ከፊት ፈረስ ከኋላ መሆንን ያሳብቃል ። የትግርኛ ቋንቋ ከኣማርኛ ቋንቋ ቀድሞ መነገር ባይጀምር ኖሮ "ኣማርኛ ቋንቋ" የሚባል ከነኣካቴው ኣይፈጠርም ነበር። ምክንያቱም የኣማርኛ ቋንቋ የተበላሸ የትግርኛ ቋንቋ ስለሆነ ፤ ወይም ትግርኛ ሲበላሽ ደንበኛ ኣማርኛ ስለሚሆን። ጥቂት ምሳሌ፦
"ብላዕ" የሚለው የትግርኛ ቃል መጥራት ያቃተው "ብላ" ይላል። ነዓ => ና ፤ ፀሓይ => ጠሃይ ፤ ኺድ => ሂድ ፤ ሓደ => ኣንድ ፤ ክልተ => ሁለት ፤ ኣርባዕተ => ኣራት ፤ ምኢቲ => መቶ ፤ ሸሓነ => ሰሃን ፤ ፀባይ => ጠባይ ፤ በዓል => በኣል ፤ ሕራእ => እራ.... ወዘተ የዚሁ ማረጋገጫዎች ናቸው።
እናም ትግርኛን የተናገረ መስሎት የትግርኛ ስብርባሪ ቃላት ክምር ኣማርኛን ከ "ነብሄሩ" ይፈጥራሉ። የኣማርኛ ቋንቋ የተበላሸ የትግርኛ ቋንቋ ነው ያልኩበት ምክንያት ለዚህ ነው።
3= ከኣክሱም ውጭ ያለው ወይም ከትግራይ ውጭ ያለው የኣማራ ህዝብ ትግርኛ መናገር ኣይችልም። ወይም ኣሁን በኣክሱም/በትግራይ ያለው የትግራይ ህዝብ ኣማርኛን እንደ ኣማራዎቹ ኣቀላጥፎ መናገር ኣይችልም። ይህ ያልኩበት ምክንያት ፦ በጥንት ዘመን ኣማራዎች ኣክሱም ይኖሩ ከነበረ እና እንደ ደብተራው ኣባባል እውነትም ኣማራዎች ከኣክሱም ወዳሁኑ የኣማራ ክልል ተንቀሳቅሰው/ተፈናቅለው/ተሰደው ከሆነ መቼም ሰው ከነባህሉና ከነ ቋንቋው ስለሚጓዝ ኣሁን በኣማራ ክልል እና በሌሎች ኣከባቢ ያለው የኣማራ ህዝብ ትግርኛን ኣቀላጥፎ መናገር በቻለ ነበር ፤ ወይም ኣሁን በኣክሱም/በትግራይ ያለው የትግራይ ህዝብ ኣማርኛን ኣቀላጥፎ መናገር በቻለ ነበር። ነገር ግን የትግራይ ህዝብ 80%ቱ ግእዝ ቋንቋ የሆነውን ትግርኛ ጥንትም ዛሬም በመናገር ላይ ነው።ይህም ማለት የኣሁኑ የትግራይ ህዝብ እና የኣማራ ህዝብ ትግርኛ እና ኣማርኛ ቋንቋዎችን እንደ ስፖርት መለዮ ልብስ የተቀያየሩ ህዝቦች እንዳልሆኑ ማረጋገጫ ነው። ጥቂት የአክሱም ነገስታት አማርኛን በሚስጥር ቋንቋን ይጠቀሙ ከነበረ የሚስጥር ቋንቋው ይጻፍበት የነበሩ ፊደላት የት ገቡ? ለምንስ የሳባና የግእዝ ፊደላት በብራና ላይ ጽሁፎች ፤ በኣርኪኦሎጂካዊ ቁፋሮዎች በየጊዜው ተቆፍረው ሲወጡ ይህ የሚስጥር ቋንቋ ይጻፍበት የነበሩ ፊደላት ግን እስከ ዛሬ ሊገኙ ኣልቻሉም። ለምን?
ስለዚህ የሰኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ግምት ምኞት ነው።
4= ሌላው የገረመኝ ነገር ደብተራው የሚከተሉትን ጥቂት የኣክሱም ነገስታት የኣማርኛ ስም ስለነበራቸው የኣማራ ህዝብ ኣክሱም ይኖር ነበር የሚል ጥርስ ኣልባ ፍልስፍና ነው፦
ለምሳሌ ደብተራው የኣማራ ስም ያላቸው የነገስታት ስም እንያቸው፦
በነገራችን ላይ በስም ከሄድን የተሳሳተ ግንዛቤ (GIGO) ላይ እንዘፈቃለን ፤ ምክንያቱም ተጋሩዎቹ እነ ልዑል መንገሻ ስዩም ፤ ራእሲ (ራስ) ኣሉላ ኣባ ነጋ ፤ ካሳ ሃይሉ ፤ ካሳ ምርጫ ፤ ዋግ ስዩም ጎበዜ ስማቸው ኣማርኛ ስለሆነ በተሳሳተ መልኩ ኣማራዎች ናቸው ልንል ነው ብቻ ሳይሆን በተቃራኒውም እነ ዳግማዊ ዘራያቆብ ፤ ሚካኤል ዓሊ ፤ ንጉስ ተክለሃይማኖት ፤ ዳግማዊ ሚኒሊክ ፤ ሃ/ስላሰ ፤ ሃ/ማርያም ደሳለኝም ተጋሩ ናቸው ልንል ነው። ምክንያቱም ንጉስ ከመሆናቸው በፊት የኣጼ ዮሃንስ ስም በዝብዝ ካሳ ምርጫ ነው። እናም ኣጼ ዮሃንስም ኣማራ ናቸው ልንል ነው። 😂
ቀዳማዊ “ሃበምሌክ” እንጂ ቀዳማዊ “ምን ትልቅ/ሚኒሊክ” የሚል በየትኛውም የታሪክ መዛግብት ኣታገኝም። “ሃበምሌክ” ማለት በእብራይስጥ ‘the son of a wise man’ ማለት ነው። ደግሞስ የእናቱ የንግስት ሣባን ስም ትርጓሜ ሳታውቅ እንዲያው በደፈና “ምንሊክ ማለት ምን ትልቅ ማለት ነው” ብሎ መዋሸት ራስን ለትዝብት ይዳርጋል። 😂
“ዘዋሬ ንብረት” የግእዝ ቃል እንጂ የኣማርኛ ቃል ኣይደለም። ትርጉሙም ተንቀሳቃሽ ግምጃ ማለት ነው።
“ግርማ ኣስፍር” የግእዝና የትግርኛ ቃል እንጂ የኣማርኛ ቃል ኣይደለም። ትርጉሙም ክብርን ጠብቅ ማለት ነው።
“ኣርፍድ” በሚገርም ሁኔታ የግእዝ እና የትግርኛ ቃል እንጂ የኣማርኛ ቃል ኣይደለም። ትርጉሙም ዘገየህ ማለት ነው። (በታሪኩ የኋለኛው ንጉስ እንደማለት ነው)።
“ወሰን ሰገድ” ማለት በሚገርም ሁኔታ የግእዝ እና የትግርኛ ቃል እንጂ የኣማርኛ ቃል ኣይደለም። ትርጉሙም የኣምላክ ምስጋና ወይም የኣምላክ ይዞታ ማለት ነው።
“ተላተም” ማለት በሚገርም ሁኔታ የግእዝ እና የትግርኛ ቃል እንጂ የኣማርኛ ቃል ኣይደለም። ትርጉሙም ተጋጭ፤ ተገጭ ማለት ነው። “ተዋጊ/ጦረኛ”ን ይወክላል።
“ኣስጎምጉም”ማለት በሚገርም ሁኔታ የግእዝ እና የትግርኛ ቃል እንጂ የኣማርኛ ቃል ኣይደለም። ትርጉሙም “ኣጉረምርም/ኣቅራራ” ማለት ነው። ተጋሩ “ሁራ 3ተ” በሚባለው ባህላዊ ዘፈን ኣሁንም ለጭፈራ ይጠቀሙበታል።
“ውድም ኣስፍር ፤ ድለ ንዓድ ወዘተ” የግእዝ እና የትግርኛ ቃል እንጂ የኣማርኛ ቃል ኣይደሉም። ስለዚህ የማይመሳሰሉ ነገሮችን ለማገናኘት ላይ ታች ማለት ኣያስኬድም።
ሌላው ቀርቶ ኣማርኛ ቋንቋ በ16ኛው መ/ክ/ዘ መነገር የጀመረው በ11ኛ መ/ክ/ዘ ካከተመው ግእዛዊው የኣክሱም ስልጣኔ ጋር ለማገናኘት የሚሞክሩት የኣማራ ልሂቃን የላሊበላን ስልጣኔን ዘለው መሆኑን ላፍታም ልብ ኣላሉትም። ታሪክ የከተበው የህዝቦቹ መስፋፋትኮ ኣማራዎች ከደቡብ ወደ ሰሜን ፤ ኣግኣዝያኖቹ ደግሞ ከሰሜን ወደ ደቡብ ኣቅጣጫ መሆኑን ኣስቀምጦታል። ኣማርኛ ቋንቋ የኣግኣዝያኑን ፊደላት ከ60 ድምፆች በላይ በኣግባቡ መጥራት ኣይችልም ፤ በኣንፃሩ ተጋሩ ግን ከ480 በላይ በሆነ ድምፅ ይጠራሉ (በኣክሱም ፤ ኣዶሊስ ፤ ቆሓይቶ እና በተለያዩ ሓውልቶች ላይ የ"ኧ ፤ ኣ ፤ አ ፤ ኧ ፤ ዓ ፤ ዐ ፤ ሀ ፤ ሃ ፤ሐ ፤ ሓ ፤ ቐ ...." ፊደላት ኣሉ)። ባጠቃላይ የኣማርኛ ቋንቋ ለኣክሱም ስልጣኔና ለግእዝ ቋንቋ ቀረቤታውም ሆነ ስልጣኔውን ለመተርጎም ከትግርኛ ቋንቋ ሲነፃፀር ኣማራዎችና የኣክሱም ስልጣኔ ሆድና ጀርባ ናቸው።
ኣማርኛ የጥንታዊት ኣኽሱም ነገስታት የሚስጥር ቋንቋ ነበረ ትላላችሁ። እኔ ደግሞ የኣኽሱም ነገስታቱ ከህዝቡ ነው የሚገኙት። ስለሆነም የጥንታዊት ኣኽሱም ነገስታት ከትግርኛ በተጨማሪም ኣማርኛን በሚስጥር ፈጥረው በ2ኛ ደረጃ ይግባቡበት ነበር ማለታችሁ ከሆነ ከተጨባጭ ታሪካዊ መረጃዎች ኣንፃር ትክክል ባይሆንም (ምክንያቱም የኣማራ ህዝብ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ብ/ብ/ሰ/ህዝቦች ተዳቅሎ የተገኘው በ12ኛው መ/ክ/ዘ/ስለሆነ) ተቃውሞ የለኝም። ምክኒያቱም ይህ የናንተ ኣነጋገር ኣሁንም ”ኣማርኛ የፈጠሩት ተጋሩ ነገስታት ናቸው” የሚል እንድምታ ስለሚሰጥ።
በነገራችን ላይ የመጨረሻዎቹ ኣኽሱማውያን ነገስታት ማለትም እነ ይምሓረነ ክርስቶስ ከፖለቲከኛውና ኣንኮበራዊው የውሸት ባለ 6 ክንፉ ተክለ ሃይማኖት/ዳግማዊ ተክለሃይማኖት እና ከይኩኖ ኣምላክ ጋር ላስታና ሰሜን ሸዋ ላይ ይገናኙና ለስልጣንም ይፈታተኑ ነበር። ወቅቱም 12ኛው መ/ክ/ዘ ሩብ ነው፡፡ ልብ በሉ ኣንባብያን~! ይህ ወቅት ሴማውያን(ተጋሩ) ከሰሜን ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ፤ ኩሻውያን (ኦሮሞዎች) ከደቡባዊ ወደ ሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል የተስፋፉበት ጊዜ ነው። እናም “የሴማውያንና የኩሻውያን ጦረኞች ሃይላቸውን ጨርሰው በያሉበት ወደተረጋጋ ኑሮ የተመልሰው ፤በጊዜ ሂደትም እየተጋቡ መኖር ጀመሩ። በዚህ ሂደት ከ2ቱም ዘሮች ጋብቻ በኋላ የተወለዱ ልጆች ኦሮምኛ ያልሆነ ነገር ግን ኦሮምኛ የሚመስል እና ትግርኛ ያልሆነ ነገር ግን ትግርኛ የሚመስል ቋንቋ(የሁለቱም ወላጆቻቸው ቋንቋ)የሚናገሩ ልጆች እየበዙ መጡ።ይህ ቅይጥ ቋንቋ “ኣማርኛ” ተብሎ ታወቀ።ይህን ተከትሎም እንደህዝብ ኣማራ የሚባል በኣዲሱ ኣማርኛ ቋንቋ የሚግባባ ህዝብ እየበዛ መጣ። ዘመኑም ከ12ኛው ምእተ ዓመት 2ኛው ኣጋማሽ ነበር” ይላል (ዋዜማ ገጽ 5 ያንብቡ።)
ስለዚህ ለልሂቃነ ሸዋዎች የምጠይቃቸው ጥያቄ፦
የትኛው የኣኽሱም ንጉስ ነው ኣማርኛ ቋንቋን የተናገረው?
ሌላው ”ኣማርኛ የጥንታዊት ኣኽሱም ነገስታት የሚስጥር ቋንቋ ነበር” ከተባለ ኣሁንም በተዘዋዋሪ የያኔ ቀዳሚው የኣክሱማውያን ቋንቋ ትግርኛ መሆኑን እየመሰከርን ነው ፤ ምክንያቱም “ሚስጥር” ማለት ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ የሚያውቁት ማለት በመሆኑ ከብዙው የትግራይ ህዝብ ጥቂት መሪዎቹ የሚግባቡበት የተለየ መግባቢያ ቋንቋ ማለት ስለሆነ ኣማርኛ ቋንቋ የትግራይ ህዝብ ቋንቋ በሆነው ሰፊው ትግርኛ ቋንቋ ውስጥ በባለስልጣናቱ ይነገር ነበር ማለት ነው።(እውነታ ባይኖረውም እንደ ደብተራው ኣነጋገር ከሆነ ማለቴ ነው) በዚህ ኣነጋገር የትግርኛ ቋንቋ ቀዳሚነትን ባይጋፋም የተጋሩ የኣክሱም ቀዳሚ ባለቤትነትን ግን ሆን ተብሎ ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት በደብተራው የተሸረበ መሰሪ ዓ/ነገር ነው።
እንዲህ ከሆነ ደግሞ ደብተራ ኣምሳሉ የምጠይቃቸው ጥያቄ “እነዚህ የኣኽሱም ተጋሩ ከየት መጡ?” የሚለው ጥያቄየ ነው መልሳቸው “ከዓረብ ሃገር/ከየመን” እንደሚሆን እጠብቃለሁኝ 😉
እነ ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን “ተጋሩ የዓረብ ዘር ናቸው ፤ ካሁኗ የመን ነው ወደ ኣክሱም ኣማራን ለማገልገል የመጡት” ብላችሁ በመጽሃፍ መልክ ለማውጣት 11ኛው ሰዓት ላይ በነበራቹበት ጊዜ ነው በድንገት ኮመዲያን ፍቅሬ ቶሎሳ “እውነተኛው የኣማራና የኦሮሞ የዘር ዝምድና” በሚል የኣዳም ጎጃሜ ነው ኣስቂኝ ደብተሩ ላይ ድንገት ክፉኛ ፉገራ “ኣማራና ኦሮሞ ኩሽ ነው” ሲል የፎገራቹህ።
በኮመዲያን ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሃፍ መሰረትና በብዙዎቹ የታሪክ ምሁራን መሰረት ኣማራና ማዳጋስካር እንጂ ኣማራና ኣኽሱም ኣልተገናኝቶም ነው ነገሩ። 😂
እናም “ተጋሩ የዓረብ ዘር ናቸው ፤ ካሁኗ የመን ነው ወደ ኣክሱም የመጡት ካላችሁ ፤ በናንተ የጥንታዊት ኣክሱም ቋንቋ ኣማርኛ ይሁን እንበል።ታድያ የኣሁኖቹ የኣረብ ህዝብና የየመናውያን ቋንቋስ ለምን ትግርኛ ኣልሆነም? 😂
የትግራይ ህዝብ ከየመን እና ከዓረብ ወደ ኣክሱም እናንተን ለማገልገል ከመጣ የኣሁኖቹ የኣረብ ህዝብና የመናውያን ለምን እንደ ተጋሩ ትግርኛ ኣይናገሩም? 😂ወይም ደግሞ ለምን የትግርኛ ፊደል ኣይጠቀሙም? 😂
በሌላ ኣነጋገር የትግራይ ህዝብ ለምን ዓረብኛ ቋንቋ ኣይናገርም? ለምንስ የዓረብኛ ፊደል በስነፅሁፉ ላይ ኣይጠቀምም? 😂
ከጥንት ከንግስተ ሳባ ጀምሮ እስከ ኣሁን በትግራይ በብራናና በሓውልቶች ላይ ተፅፈው ያሉት በሳባና በግእዝ ቋንቋ እንጂ በዓረብኛ ኣልያም በኣማርኛ ፊደላት ኣይደሉም 😎
እነ ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን የሰውን ማንነት ብቻ ቀምተውና ዘርፈውም ኣልረኩም ፤ ይልቁንም የቀሙትን ማህበረሰብ ተቀማሁ፤ ተዘረፍኩ ብሎ በመረጃ እንዳይሞግታቸውም እንደ ኣሸን በሚበዙ የውሸት የታሪክ መጽሃፈ ድሪቶዎቻቸውም ጭምር ላለፉት 130 ዓመታት ኣስደግመው ከትበውታል ፤ የኣሁኑ የነሱ ትውልድም በመሰሪ የታሪክ ድሪቶዎቻቸው ተብትበውታል ፤ የነበራቸውን ስልጣን ተጠቅመውም በትግራይ ስለተጋሩ ማንነት ፤ ባህል ፤ ወግ እና ስልጣኔ የሚያወሱትን ጥንታዊ የብራና መፃህፍቶቻችን ፤ እውነተኛ የቅዱሳን ድርሳነ ገድሎቻችን እና ወርቃማ ቅርሶቻችን ዘርፈው ወደ ኣንኮበር ወስደዋቸዋል ፤ ኣሁንም በማ/ቅርሱሳን ኣባላት በኤግዚብሽን ስም እያጓዟቸው ይገኛሉ።
በኣሁኑ ሰዓት ከከፍተኛ የት/ት ተቋማት የመቐለ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ፡ በታሪክ ፤ በትያትርና በስነ ስእል ፤ በዘጋቢነት ፤ በስነ ቋንቋ እና በመሰል የማህበረሰብ ዘርፎች የት/ት ክፍሎች ተምሮ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ ለመውጣት ተማሪዎች ኣማራነት የሚያንጸባርቅ የመመረቂያ ጽሁፍ ማዘጋጀት ግድ ይላቸዋል። ካልሆነ ግን የመመረቂያ ጽሁፋቸው በgood ግሬድ ያልፋል ፤ ኣልያም delay ይባላሉ።
ይህም የኣማራ መምህራኑ ያልተገኘው ማንነትታቸውን የነበረና ጥንታዊ ለማስመሰልና በወጣቱ ትውልድ ኣእምሮ ላይ ኢትዮጵያዊነትየኣማራነት መሆኑን የማስረጽ ተልእኮን ለማሳካት የሚደረግ የረጅም ጊዜ እቅድ ሩጫ ነው።
እንደሚታወቀው ኣማራ ማለት ሃይማኖት ያልነበራቸው የተለያዩ ብ/ብ/ሰ/ህዝቦች በተጋሩ ክርስትና ተጠምቀው ተጋሩን ከማገልገል ነፃ ይሆኑ ዘንድ ሲፈቀድላቸው የሚሰጥ የተለያዩ የብሄር ጥርቅም መጠሪያ ነው ። ኣማራ የሚባል ህዝብ እንጂ ኣማራ የሚባል ብሄር ኣልነበረም ፤ የለምም። “አማራ ከየጎሳው የተጠራቀመ የወታደር ቡድን እንጂ ‘አማራ’ የሚባል ራሱ የቻለ ህዝብ የለም” (ፕ/ር ሃይሌ ላሬቦ)
“የኣማራ ህዝብ በ13ኛው መክዘ ከሰሜንና ከደቡብ ኣቅጣጫዎች ይስፋፉ በነበሩ 2 በዘር የተለያዩ ህዝቦች ወታደሮች ድቅለት ምክንያት የተገኘ ህዝብ ነው።” (ፕ/ር ባየ ይማም)
“ኣማራነት ክርስትናን ስትቀበል የሚሰጥህ ማንነት ነው”(ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)
“ኣማራነት ብሄር ያልሆነበት ዋናው ምክንያት በ12ኛው መ/ክ/ዘ ሩብ ዓመት ህዝቡ በዚሁ የውህደት ሂደት ከሁሉም የሴም ብሄሮችና ከሁሉም የኩሽ ብሄሮቸ ተዳቅሎ የተገኘ ህዝብ ስለሆነ ነው።” (ፕ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት)
“ኣማራነት ወይ የትግራይ ዘር ኣልሆነ ወይ የኦሮሞው ዘር ኣልሆነ ወይ የጉራጌው ዘር ወይ የወላይታው ዘር ወዘተ ዘር ብቻ ያልተገኘ ኣማራነት ስለሆነ የኣማራ ህዝብ ይባል እንደሆነ እንጂ የኣማራ ብሄር ለማለት ይከብዳል”
(“የአማርኛ ሰዋስው”ገጽ 4-5) 😂
የኣጼ ዮሃንስ የስራ ቋንቋ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ መቐለ በሆነበት ዘመን ትግርኛ ለመሆኑ ኣያጠራጥርም ፤ ምክንያቱም ኣሁን የመቐለም የኣክሱምም ህዝብ ኣማርኛን ኣቀላጥፈው መናገር ኣይችሉም። ይህ ማለት ግን ትግርኛ ከኤርትራና ትግራይ ውጭ ይነገር ነበር ማለት ኣይደለም። ምክንያቱም ኣጼ ዮሃንስ የብሄርተኝነት ችግር (identity crisis) ሳላልነበረባቸው በ 1 ሃይማኖት የሚያምኑ ፌዴራሊስት ንጉስ እንጂ በ1 ቋንቋ የሚያምኑ ዓፋኝ ንጉስ ኣልነበሩም።
ዋና ነጥቡ ያማራ ህዝብ ኣክሱም ከነበረ፡ መቸም ሰው ሲሰደድ ከነቋንቋው ከነ እምነቱ ከነ ስነጽሁፉና ይገለገልባቸው ከነበሩ ቁሳዊና መንፈሳዊ ሃብቱ ጋር ነው እሚሰደደው ።ታድያ የኣማራ የቤት ኣሰራር ከሳርና ከእንጨት ፤ ኣነጋገራቸውም ከኵሽ እና ከሴም ፤ ኣለባበሳቸው ኣመዛኙ የኩሽ ሆኖ ሳለ ኣማራነት እና ኣኽሱምነት ውሃና ዘይት ኣይሆንም? 😂
ባጠቃላይ ኣማራነት ከኣክሱማውያን ጋር ምንም የሚያመሳስል ነገር የለውም 😂
ስለ ኣማርኛ ቋንቋ ኣፈጣጠር፦
================
እንደ ፕሮፌሰር ባየ ይማምና ሌሎቹ የሥነ ልሳን ምሁራን አማርኛ የተወለደው በ13ኛው መክዘ(ከ800 ዓመት በማይበልጥ ዘመን ማለት ነው) የኣክሱም ስረው መንግስት መዳከምን ተከትሎ በሴማውያን መሪዎችና በካማውያን (ኩሻውያን) ወታደሮች መካከል በተፈጠረው የጋብቻ ግንኙነት ሳቢያ ቋንቋዎቻቸው በመደባለቁ ነው። ስለሆነም አማርኛ የ13ኛው ክፍለ ዘመን ቅይጥ ቋንቋ (pidgin)እንጂ እንደ ግእዝ ፡ትግረና ትግርኛ ንጹሕ ሴማዊ ቋንቋ አይደለም። ምክንያቱም ኣማርኛ 15% ኣከባቢ ብቻ ግእዝ ሲሆን ትግርኛ ግን ከ75% እስከ 85%ቱ ግእዝ ነው። ለዚህም ነው ልክ እንደ ግእዝ ትግርኛ
“ኧ ፤ ኣ ፤ አ ፤ ኧ ፤ ዓ ፤ ዐ ፤ ሀ ፤ ሃ ፤ሐ ፤ ሓ ፤ ሰ ፤ ሠ ፤ ፀ >> ን እና ቐ ቑ ቒ ቓ ቔ ቕ ቖ ቘ ቚ ቛ ቜ ቝ; ኸ ኹ ኺ ኻ ኼ ኽ ኾ ዀ ዂ ዃ ዄ ዅ;ኲ ኳ ኴ ኵ;
ጐ ጒ ጓ ጔ ጕ” የመሳሰሉትን በየራሳቸው የድምጽ ኣወጣጥ ሲጠቀም እሚስተዋለው። ኣማርኛ ግን እነዚህን ልሳናት ኣያወጣም ፤ ኣይጠቀምም። ለምሳሌ ያህል ኣማርኛ መሠረታዊ ቃላት ሳይቀሩ ከኩሽ (ካም)የተዋሳቸው ናቸው። ምሳሌ፡- ውሃ ፣ ውሻ ፣ ሰንጋ ፣ ወዘተ. ግሱ በዓረፍተ ነገር መጨረሻ ላይ ስለሚመጣ የዓረፍተ ነገር ቅርጹም ሴማዊ አይደለም፡ይላሉ ፕሮፌሰር ባየ ይማም ።
(“የአማርኛ ሰዋስው”ገጽ 4-5)
ታድያ ሰዎቹስ(ኣማራዎችስ) ከየት ተገኙ? ለሚለው ጥያቄ ኣጭር መልስ፦
“ቋንቋ የሰዎች መገኘት ተከትሎ የሚመጣ የሰዎቹ መግባቢያ ነው” ይሆናል 😂
ይህም የቋንቋው ኣመጣጥ ብቻ ሳይሆን የሰዎቹም(ኣማራዎች) የኩሽ(ካም) እና የሴም ቅይጥ እንደሆኑ ኣመጣጣቸው ፍንትው ኣድርጎ ኣዙሮ እየመሰከረልን ነው።
የላይኛውን የፕሮፌሰር ባየ ይማም ኣንቀጽ በጥሞና ለኣንድ ኣፍታ ደግማችህ ኣንብቡትና ስለ ኣማራነት እና ኣማርኛ ግልፅ ይሆንላችኋል።
ከ13ኛው መክዘ በፊት ግን (ከ4000 ዓመታት ጀምሮ ማለት ነው ) የኣክሱም ሳባውያን (ኣግኣዝያን) እና ኩሻውያን (ካማውያን) ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ ኢትዮጵያ ቀድመው እንደገቡ መጽሓፍ ቅዱስም ሆነ ኣሁን በኣርኪኦሎጂካዊ ቁፋሮዎች የተገኙ ዕጹብ ድንቅ የማያወላዱ እንቅጭ መረጃዎች ኣፍ ኣውጥተው ስለ ኣግኣዝያን ትግራይ ትግርኚ ጥንታዊነት እየመሰከሩ ነው።
ማረጋገጫው ከፈለጋችሁ፦
በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ “ኢትዮጵያ” የምትባለው ከግብጽና ከሊብያ በስተደቡብ ያለች በደቡብ እና በምእራብ ወሰኗ ያልተገለጸ ሰፊ የዓለም ክፍል ናት።
ኢትዮጵያ ፤ ግብፅ እና ሊብያ ወሰንተኞች እርስበርስ የተገዛዙ ናቸው የሚያሰኛቸው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ጦር ማዝመታቸው፤ መሪዎችም አንዳድ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ሌላ ጊዜ ግብጻዊ መባላቸው ነው። 2ነገ 19፡9፤ 2ዜና 12፡2-9፤14፡9-13፤16፡8 ኢሳ 37፡9። እናም ከነገደ ካም ኩሻውያን የአባይን ወንዝ በመከተል በሰሜን፣ በምራብና በደቡብ በኩል ዘልቀው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ሠፈሩ።አምልኮታቸውም በወንዝ፣ በኩሬ፣ በሐይቅ፣ በተራራ፣ በእንሥሳት፣ በአራዊት፣ በአዕዋፍ፤ በዛፎች፤ እንደነበር ይተረካል ምልክቱም እስከዛሬ ድረስ ይታያል።
ኣክሱምን ሃያል ሃገር ኣድርገው የመሰረቷት ግን ሴማውያን( ሳባውያን) ናቸው።በምሥራቅ እና በሰሜናዊ ምሥራቅ በኩል ገብተው ሠፈሩ።አምልኮታቸው በጸሐይ በጨረቃና በከዋክብት ነበር።
በኋላ ከኩሻውያን ጋር ተዋግተው እራሳቸውን ነጻ ካወጡ በኋላ “አጋዝያን” ተባሉ። ቋንቋቸውም ግእዝ ነበር። እየተደራጁ ሲሄዱም የኩሻውያንን መንግሥት ደምሥሰው የራሳቸውን መንግሥት የሳባውያንን መንግሥት አቋቋሙ።
ሳባውያን ከሊብያና ከግብጽ በስተደቡብ የተንጣለለው ሰፊ በርሃ ተጨምሮ ተራራማዋ የአገራችን ክፍል ሁሉ በንድነት “ኢትዮጵያ” እየተባሉ ሲጠሩ የነበሩ ሲሆን መቼ እንደተለያዩ በትክክል ሳይታወቅ “የኑብያ ኢትዮጵያ እና የሳባ ኢትዮጵያ” መባል ጀምረው በነዚህ ስሞች እየተጠሩ ባለበት ጊዜ ክርስትና ተሰበከ። ሳባውያን በቋንቋ፣ በባህል፣ በታሪክና በመልካአ ምድር ከግብጽ ጋር ተቆራኝታ ለተገኘችው ለኑብያ ኢትዮጵያ ወንጌልን የሰበከላት ወንጌላዊው ፊልጶስ ነበር። ይህችውም የአሁንዋ ኢትዮጵያ ግዛት ስለነበረች ክርስትና ከዚያb ወደዚህም ተሻግሮ ነበር።
በዚህች አገር ወንጌል በ34 ዓ.ም. ተሰበከ ቤተ ክርስቲያንም በ56 ዓ.ም.ተቋቋመች። በ1100 ዓ.ም. በሙስሊም ወራሪዎች ተደመሰሰች። በአሁንዋ ኢትዮጵያ የነበረች ቤተ ክርስቲያን ግን አልተደመሰሰችም። የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ያስፋፋትና ወንጌልን የሰበከላት ግሪካዊው አባ ሰላማ ነው ዘመኑ ከ318-330 ዓ.ም.ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።
በእርሱ አገልግሎት፦
= ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት የተባለች ቤተ ክርስቲያን ተመሠረተች
= የጸሎት ቤተ ተሠራ
= መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ግእዝ ተተረጎመ
= ቤ/ ክር በኢትዮጵያ መስፋፋት ጀመረች።
የሳባውያን ኢት/ያን ያዘመኗት ኣግኣዝያን ግን ምንም እንኳ በሰሜንና በምስራቅ ኣፍሪካ ላይ ተወስነው ይኖሩ የነበሩ ህዝቦች ቢሆኑም፡ መካከለኛው እንዲሁም የመንን ጭምር ያስተዳደሩና ወዳሁኗ ኢት/ያ ቀድመው የመጡ ህዝቦች ናቸው።
(የኣጼ ካሌብና የልጃቸው ኣጼ ገ/መስቀል ገድለ ታሪካቸውን ኣንብ)
ሌላው በአሁኑ ሰአት በኣክሱም ዙሪያ “ከ200” በላይ የቆሙና የወዳደቁ ሓወልቶች አሉ።
ማለቂያ አልቦ የሸክላና የጥበባዊ ስራዎች ስብርባሪዎች..መቃብሮች..የነገስታት አጽሞች ፍርስራሽ ቤተመንግስቶች ጽሑፎች ድርሰቶች ፊደሎች ዜማዎች አሃዞች ቤተመቅደሶች ኧረ ስንቱ በአክሱም ዙሪያ ተትረፍርፈው ይገኛል 😂
እነዚህ በሙሉ(100%) የአግኣዚያን(ሳባውያን) ቅሪቶች ናቸው! ጽሁፎቹ በሙሉ የሳብያውያን ነው።
ነገደ ኩሽ ጥንት በኢትዮጵያ(በአክሱም ዙሪያ) ስለመኖሩ ቢረጋገጥም ነገር ግን የአለም አርኪኦሎጂስቶችና የታሪክ ተንታኞች እስካሁን ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ምርምር “ኩሽ “ምን ምን እንደሰራ የሚገልጽ “አንዲት ሰባራ ገል” እንኳ ሊያገኙ በፍጹም አልቻሉም!
አንዲት ሰባራ ገል እንኳ! 😂
ሁሉም ቅርስ የአግኣዚያን(ሳባውያን)ትግራውያን) እንደሆነ ብቻ ነው እስካሁኗ ቅጽበት ታሪክ የሚያዉቀው።እነዚህ ኣርኪኦሎጂካዊ ማስረጃዎች ስለኩሽ ቋንቋም ሆነ ነገድ እስካሁን ኣንድም እደግመዋለሁ ኣንድም መረጃ ኣያሳዩም።ሁሉም የሳባውያንና ኣግኣዝያን ጥበብ ብቻ በቃ ሁሉም የሳባውያንና ኣግኣዝያን ጥበብ ብቻ ይመሰክራሉ።
ከለዚህም ነው ተጋሩ ንጹህ የሴም ሳባውያን(የሳባ የቀዳማዊ ሚኒሊክ) የቦኩር ልጆች ናቸው፡ እሚባለው። 😂
ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ኣረጋው ይህቹንም ውሰዳት፦
“ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ሀገሮች የተለየ የሚያደርጋት የጽሕፈት ሥርዓት ከሴማውያን ቋንቋዎች የተገኘ ነው። ከሌሎቹ ቋንቋዎች ሲወዳደር ስለ ሳባውያን ሴማዊ ቋንቋዎች አመጣጥ በድፍረት መናገር ይቻላል። ምክንያቱም በሰሜን ኢትዮጵያ(ኣክሱምና ኤርትራ) ድንጋይ ላይ የተቀረጹ የሳባውያን ሴማዊ ቋንቋዎችን አመጣጥ ጽሑፎችና ሌሎችም ማስረጃዎች ስላሉ ነው።”
(የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና ቋንቋዎቻቸው አጭር ቅኝት ገጽ 2-3)። 😂
“በግምት የዛሬ 4 ሺህ ዓመት በሳባውያን ቋንቋና በጊዜው ሰሜን ኢትዮጵያ ይነገሩ በነበሩ ቋንቋዎች ዘገምተኛ ውኅደት ግዕዝ ሊወለድ በቃ። ግዕዝ የአክሱም ዘመነ መንግሥት ቋንቋ ሲሆን እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ዋነኛ የመግባቢያ ቋንቋና ልሳነ ንጉሥ ነበር። ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ግን ሙሉ በሙሉ መነገር አቆመ።”
(የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና ቋንቋዎቻቸው አጭር ቅኝት ገጽ 3-4)።
ይሄ ነው ታሪካችን፡ወንድሜ። 😂
ከላይ የጠቀስኳቸው ሁሉ ነገስታት ከዳኣማታውያን እሰከ የሓ እና አክሱም ስርወ መንግስት ሲነግሱ እና ለአራት ሺሕ ዘመናት ያህል የዓለማችን ኃያላን ሁነው ሲያስተዳድሩ ፤ በስነ ሕንጻ ሲራቀቁ ፤ ቆዳ ኣልፍተው ብራና ሰርተው መጻሕፍትን ሲጽፉ፤ፊደልን ቀርጸው መዛግብትን ሲያዘጋጁ ፤ ዜማን ቀምረው ግዕዝ ፤ እዝል ፤ አራራይ ፤ ድጓ ፤ ጾመ ድጓ ሲፈጥሩ ከግብጽ እሰከ ደቡብ ዓረቢያ ግብር ሲያስገብሩ ፤ ከምኩራብ እስከ ቤተክርስቲያን በመጨረሻም መስጂድ ዓል ነጃሺን ሲያንጹ ያኔ የአማራ ልሂቃኖች ኣሁን ትግራዋይ ለመሆን የሚመኙት እና ኣሁን ትግራይን የሚሳደቡት ሰዎች የት ነበሩ?
“አማርኛ ፡ ልሳነ-ጽሑፍ ፡ መሆን ፡ የጀመረው ፡ በ14ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ላይ ፡ ሲሆን ፡ ይህንንም ፡ ያደረገው ፡ ሁሉንም ፡ የግዕዝ ፡ ፈደላትን ፡ በመውሰድና ፡ 6 ፡ አዳዲስ ፡ የላንቃ ፡ ፊደላትን ፡ ማለትም ሸ ፣ ቸ ፣ ኘ ፣ ዠ ፣ ጀ ፣ ጨ እና ፡ ኸን ፡ በመጨመር ፡ ነበር። ነገር ፡ ግን ፡ በጽሑፍ ፡ ይበልጥ ፡ መስፋፋት ፡ የጀመረው ፡ ከአጼ ፡ ቴዎድሮስ ፡ ጀምሮ ፡ ሲሆን ፡ ለዚህም ፡ በተለይ ፡ አስተዋጽኦ ፡ ያደረገው ፡ ጸሐፊያቸው ፡ ደብተራ ፡ ዘነብ ፡ ነው።”
(ጳውሎስ ኞኞ፣2003፣ አጤ ምኒሊክ በሀገር ውስጥ የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎች፣ አዲስ አበባ አስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት)
‹‹በ13ኛው መክዘ የይኩኖ ኣምላክ መንገስ የአኩስም መንግሥት ጠንካራ መሠረት ከሆነው የዛሬው ኤርትራና ትግራይ አካባቢ ይልቅ ደቡቡን በመጠቀም ጠንካራ አጋርና መሠረት ለማግኘት ባደረገው ጥረት አማርኛ ተናጋሪዎቹ የመንግሥቱን ቦታ እያገኙ ሲመጡ አማርኛም መነገር ጀመረ፡፡››
( ባየ፣ 2000፣xvii-xviii፤ Girma, 2009,210)
የሚገርመው ተረተኛው ሠኣሊ ደብተራ ኣምሳሉ ገ/ኪዳን ኣረጋው የተጠቀመባቸው የመጻህፍት ማስረጃዎች ኣንድም ቢሆን የለውም  😂
(በልፍዓተይ ተስፋ)

No comments:

Post a Comment

Quick Guide to Every Herb and Spice in the Kitchen – በማድቤት ውስጥ የእያንንዱ ቅጠል እና ቅመም ፈጣን መመርያ

ደረቅ ቅጠሎች እና ቅመሞች አሳፎቲዳ (አሳፌቲዳ) – አሳፎቲዳ በህንድ አመጋገብ ውስጥ የምግብ መፈጨትን ለመርዳት የሚጠቅም ሲሆን የበሰለ ዝንጅብል ሽንኩርት ቃና ያለው ጠንካራ ሽታ አለው፡፡ አቾቴ ማጣበቂያ እና ዱቄት ...