Tuesday, April 14, 2020

መባዓ ጽዮን

መባዓ ጽዮን

Jump to navigationJump to search
መባዓ ጽዮን በሌላ ስማቸው ተክለ ማርያም በዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን የነበሩ ጻድቅ ሰው ሲሆኑ በተወለዱ በ፸፬ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል። ገድላቸው እንደሚጠቅሰው በሸዋ ግዛት አንዳገብጣን ይባል እነበር ቦታ ከአባታቸው ሀብተ ጽዮንና እናታቸው ጽዮን ትኩና በስለት ተወለዱ። ቀጥሎም ከአባታቸውና ከተለያዩ ቀሳውስት ትምህርት በመቅሰም አድገው እራሳቸውን በጾምና ጸሎት በማነጽ ቅድስናን አግኝተዋል። በዚህም መካከል ወደ ዳሞት በመሄድ ገብረ ክርስቶስ ለሚሰኙ ቄስ ጋር በ እንግድነት ከቆዩ በኋላ ሲመለሱ አደገበት አገር አባ ገብርኤል በተባሉ አስተዳዳሪ የቅስና ሹምትን አገኙ ከዚያም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት በተመሠረተው ደብረ ሊባኖስገዳም ላይ ትንሽ ጊዜ አሳልፈዋል፣ ጋፋት ይባሉ የነበሩ ሕብረተሰቦችም ክርስትናን እንዲቀበሉ ብዙ ጥረት አድርገዋል። መባዓ ጽዮን ይኖሩበት የነበረውን ዘመን ማወቅ የተቻለውም እኒሁ ጋፋቶች ከዓጼ ዘርዓ ያዕቆብ ስጦታን ለማግኘት ሲጓዙ መንገድ ላይ ይሰብኳቸው እንደነበር ግድሉ ላይ በማስፈራቸው ነው። [1]
ባጠቃላይ፦ መባዓ ጽዮን (ተክለ ማርያም) ፵፯ ዓመት በድቁና፣ ፱ ዓመት በቅስናና ፱ ዓመት በምንኩስና ሕህይወታቸውን አሳልፈዋል። ከዚህ ዓለም ከተለዩ በኋላ አንድ ተከለ ሃይማኖት የተባለ ሃብታምና ሚስቱ ወለተ ጽዮን ከጻድቁ ገድል በረከት እንዲያገኙ በማሰብ የመባዓ ጽዮንን ታሪክ "ገድለ መባዓ ጽዮን" በሚል መጽሐፍ ምክሖ ጊዮርጊስ በተባለ ፀሐፊ እንዲጻፍ አደረጉ። ይህ መጽሐፍ እጅግ በተዋቡ ደማቅ ስዕሎች ያሸበረቀ ሲሆን ሰአሊው "ኢግናጢየስ" የሚባል ሰው ሊሆን ይችላል በማለት ታሪክ ተመራማሪው ዋሊስ በጅ ገምቷል [2] ይህ መጽሐፍ በዓፄ ቴወድሮስ መቅደላ ላይ ሊያሠሩት ለነበረው ቤ/ክርስቲያናቸው እንደስጦታ አዘጋጅተውት በመሃሉ በእንግሊዞች ተወድሶ እንግሊዝ አገር ውስጥ ይገኛል።

ከገድለ መባዓ ጽዮን የተወሰዱ ጥንታዊ ስዕሎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]



ማጣቀሻወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ ገድለ መባዓ ጽዮን
  2. ^ Budge, Wallis. The lives of Mabâ' Sĕyôn and Gabra Krĕstôs. The Ethiopic texts ed. with an English translation and a chapter on the illustrations of Ethiopic mss. (1898)

No comments:

Post a Comment

Quick Guide to Every Herb and Spice in the Kitchen – በማድቤት ውስጥ የእያንንዱ ቅጠል እና ቅመም ፈጣን መመርያ

ደረቅ ቅጠሎች እና ቅመሞች አሳፎቲዳ (አሳፌቲዳ) – አሳፎቲዳ በህንድ አመጋገብ ውስጥ የምግብ መፈጨትን ለመርዳት የሚጠቅም ሲሆን የበሰለ ዝንጅብል ሽንኩርት ቃና ያለው ጠንካራ ሽታ አለው፡፡ አቾቴ ማጣበቂያ እና ዱቄት ...