Saturday, April 4, 2020

ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና (COVID-19) የካንሰር ህመምተኞች


የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና (COVID-19) የካንሰር ህመምተኞች ማድረግ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
***
የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ሰአት አለማችንን ክፉኛ እየፈተናት ሲገኝ ይህ ጽሁፍ እስከተዘጋጀበት ሰአት ድረስ (23/3/2020 320PM CAT) 188 ሀገራት 350,646 ሰወችን በሽታው ሲያጠቃ፤ 15,317 ህይወታቸውን አጥተዋል 100,362 የሚሆኑቱ ደግሞ ከህመማቸው አገግመዋል፡፡ በቅደም ተከተል ቻይና፡ ጣሊያን፡ ስፔን፡ አሜሪካና ኢራን ደግሞ በወረርሽኙ ክፉኛ የተጠቁ ሀገሮች ናቸው፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም እስካሁን 11 የተረጋገጡ COVID-19 ህመምተኞች ተገኝተዋል፡፡ እልህ አስጨራሽ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም የወደፊቱን አሁን ላይ ሆኖ መተንበይ አሰቸጋሪ ነው፡፡
በመላው ዓለም የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎችም በእንደዚህ አይነቱ አሰቸጋሪ ወቅት የፊት ተሰላፊዎች፤ የሀገራቸውና የወገናቸው አለኝታ በመሆን የራሳቸውን ህይወት ጭምር አሳልፎ እሰከመስጠት የሚደርስ መስዋትነት እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ወቅት ታዲያ የካንሰር ታማሚወች መረዳት የሚገባቸውን እውነታዎችና ማድረግ ስለሚገባቸውን ጥንቃቄዎች ማሳወቅ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የዛሬው ጽሁፌም በዚህ ላይ ያተኮረ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ኮሮና የቅርብ ጊዜ ችግር እንደመሆኑ መጠንና አስተማማኝ የሆኑ መረጃወች እጥረት ስላለ ይህ ጽሁፍ የተዘጋጀው ጥቂት የሚባሉ ሳይንቲስቶችና መመሪዎችን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ ውድ ተከታታዮቼ ጽሁፌን በዚህ መንፈስ እንድታነቡት ግንዛቤ ለማስያዝ እወዳለሁ፡፡
👌የካንሰር ህመምተኞች ለኮሮና ወረርሽኝ የበለጠ ተጋላጭ ናቸውን?
ከቻይና የተገኙ የተወሰኑ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የካንሰር ህመምተኞች በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ከሌሎች ሰወች ጋር ሲነጻጸሩ 3.5 እጥፍ የበለጠ ህመሙ የከፋ እንደሆነ ያሳያል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የካንሰር ታማሚዎች በኮሮና ቫይረስ የመያዝ እድላቸውና ህመሙም የከፋ የመሆን እድል አለው፡፡
👉ኬሞቴራፒ ወይም የጨረር ህክምና እየወሰዱ ያሉ ህመምተኞች
👉የደምና የንፍፊት ካንሰር መልቲፕል ማዬሎማ (Leukemia, lymphoma or multiple myeloma) ታማሚዎች
👉ኢሚዩኖቴራፒና (immunotherapy) የተወሰኑ አዳዲስ መድሀኒቶችን (targeted treatments ለምሳሌ protein kinase inhibitors (PKI) እና PARP inhibitors) የሚወስዱ ህመምተኞች
👉ባለፉት 6 ወራት ውስጥ የመቅኔ ንቀለ ተከላ የተደረገላቸው ወይም የሰውነትን መከላከያ አቅም የሚያዳከሙ መድሀኒቶችን በመውሰድ ላይ የሚገኙ ህመምተኞች
👉ከካንሰሩ በጨማሪ ተጓዳኝ ህመሞች (ለምሳሌ የልብ ወይም የሳንባ ችግር) ያለባቸው ታካሚዎች
👌የካንሰር ህመምተኞች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?
የካንሰር ህመምተኞች ለኮሮና ቫይረስ ያላቸውን ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚከተሉት ጥንቃቄዎች ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
👉በተጨማሪም የካንሰር ህክምናን ማቆም ስለማይቻል የጤና ተቋማትም ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
👉መረጋጋትና መደረግ የሚገባቸውን ትንቃቄዎች ብቻ ማድረግ
👉መረጃዎችን ሲቀበሉ ከአሳማኝ ምንጮች መሆናቸውን ማረጋገጥ
👉የኮሮና ተጋላጭነትን መቀነስ፡
👉እጅን በተደጋጋሚ በሳሙና መታጠብ
👉የእጅ ንጽህና መጠበቂያ (ሳኒታይዘሮችን) በአግባቡ መጠቀም
👉ሰው ከሚበዛባቸው ቦታዎች መራቅና ጠያቂወችን ያለማብዛት
👉አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ቤት መቀመጥ፤ ስራን በቤት ውስጥ ማከናዎን፤ በመንገድ ሲሄዱም ሆነ ሰዎች ጋር ከተቀላቀሉ ደግሞ 2 -5 ሜትር እርቀትን መጠበቅ ያስፈልጋል
👉የኮሮና ምልክቶች (ሳል፤ ትኩሳት፤ ራስምታት) ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር አለመቀላቀል
👉ከሀገር ሀገር የሚደረጉ ጉዞወችን ማቆም ወይም መቀነስ
👉የኮሮና ህመም ምልክቶች ከታዩብን በተቻለ ፍጥነት የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ ሀኪም ቤት መሄድና በሽታው ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳይሰራጭ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ
👉አላሰፈላጊ የሆኑ የሆስፒታል ጉብኝቶችን ማሰወገድ
👉የካንሰር ህክምናቸውን በተመለከተ ከሚከታተላቸው ሀኪም ጋር ሳይመካከሩ ምንም አይነት ለውጥ አለማደርግ፡፡ ነገር ግን የሆስፒታል ጉብኝትን ወይም የቆይታ ጊዜን የሚያሳጥሩ አማራጮች ካሉ ከሀኪምዎ ጋር ምክክር ያድርጉ፡፡
👉የሆስፒታል ቀጠሮ ካለወት ከተቀጠሩበት ሰዓት ቀድመውም ሆነ ዘግየተው አለመሄድ
👌የካንሰር ህመምተኞች የፊት መሸፈኛን (ማስክ) ማድረግ አለባቸውን?
እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ የካንሰር ህመምተኞች ማስከ ማድረግ እንዳለባቸው የሚያሳይ መረጃም ሆነ መመሪያ የለም፡፡ ሆኖም የአለም የጤና ድረጅትን (WHO) ሌሎች እንደ የአሜሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (CDC) ያሉ ታላላቅ አለም አቀፍ ድርጅቶች ካንሰርን ጨምሮ ለማንኛውም ህመምተኛና የጤና ባለሙያዎች የሚሆኑ መመሪያዎች ስላላቸው እነዚህን ተገባራዊ ማድረግ ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ያደጉትን ሀገራት ጨምሮ እየተፈታተናቸው ያለውን የማስከና ሌሎች ራስን መከላከያ ግብአቶች በመሆኑ፤ የተረጋገጠ የኮሮና ቫይረስ ላለባቸው ሰዎች ብቻ መስጠቱ አሁን ላይ ሁሉንም የሚያስማማ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም የህመሙን ስርጭት ለመቀነስ ሚደረገውን ጥረት ከማገዙም ባሻገር እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት ያሉንን እጅግ ውስን የህክምና ግብዐቶች በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል፡፡
ለሌሎችም መልዕክቱን ያጋሩ።
አመሰግናለሁ።

👌 the caution of Corina Virus (Covid-19) cancer patients should be careful *** This article is now trying to test our world at this time (23/3/2020 pm cat) in 188 countries, 350,646 people have lost their lives, 15,317 and 100,362 people have lost their lives, 320 and 100,362 are also from their pain. - Year-old. Follow China, Italy, her name, America and Iran are also the worst countries that are affected by the attack. The Covid-19 diseases have been found in our country Ethiopia. Even though the effort is being done, it is difficult to take the future now. Medical professionals in the whole world are paying a sacrifice to give their own life to their country and their people. At this time, I believe it is appropriate to know the facts that cancer patients should understand and do. Today's text will be focused on this. But because there is a shortage and reliable information that is a problem, this article is based on a few scientists and guidelines. So my dear followers I would like to have awareness to read my text in this spirit. 👌 are cancer patients more exposed to coronation and invasion? It shows that some information from China is worse than 3.5 times when cancer patients are caught in Corinthians and virus. Below is the chance to catch cancer patients with coronation and virus and the pain is worse. 👉 the sick people who are taking chemistry or laser treatment 👉 blood and pressure cancer, Maltipl Maeloma (Leukemia, lymphoma or multiple myeloma) patients 👉 👉 (Immunotherapy) some new medicine (targeted treatments for example protein kinase inhibitors (pki) and parp inhibitors) 👉 sick people who have been able to take medicine in the past 6 months or take medicine for body defense in the past 6 months 👉 patients who have a lot of pain (e.g. heart or heart problem) 👌 what do you expect to do with cancer sickness? Cancer patients should be careful to reduce their conflicts for coronation and virus. 👉 also, because it is impossible to stop cancer, health institutions should make pre-preparation for this. 👉 only to make stability and stability 👉 make sure that they are from the sources when they receive information 👉 reduce coronation and fight. 👉 wash your hand often with soap 👉 Hand Cleaner (Sanitizer) properly use 👉 don't have a lot of places where people are too much. 👉 unless it is necessary to sit home, do work at home, when they go on the road or join people, you need to wait from 2 meters. 👉 Corinthians (Sal, fever, heads) not join with people who show them 👉 stop or reduce travel from the country 👉 be careful to go to the doctor's house to go to the doctor's house and the disease should not spread to other people. 👉 removing hospital tours 👉 I don't make any change with the doctor who is following their cancer treatment. However, if there are any options that make a hospital visit or a long time, discuss with your doctor. 👉 if the hospital appointment is not late or late, it is not late. 👌 cancer patients should make a face cover (Mask)? There is no information or guidance that shows that cancer patients should be able to heal until now. However, it is possible to do these great international organizations, including the great international organizations, including cancer and health professionals, including the great international organizations, including cancer and health professionals. It is also a matter of fact that we are being released, including the countries that are being released, it is a matter of fact that it is a matter of fact that it is a matter of fact that it is a matter of fact. This is also possible to use the most limited medical supplies to the countries that are in Ethiopia like Ethiopia.

No comments:

Post a Comment

Quick Guide to Every Herb and Spice in the Kitchen – በማድቤት ውስጥ የእያንንዱ ቅጠል እና ቅመም ፈጣን መመርያ

ደረቅ ቅጠሎች እና ቅመሞች አሳፎቲዳ (አሳፌቲዳ) – አሳፎቲዳ በህንድ አመጋገብ ውስጥ የምግብ መፈጨትን ለመርዳት የሚጠቅም ሲሆን የበሰለ ዝንጅብል ሽንኩርት ቃና ያለው ጠንካራ ሽታ አለው፡፡ አቾቴ ማጣበቂያ እና ዱቄት ...