Thursday, April 23, 2020

Berbere

You will not get very far in your Ethiopian cooking without this mainstay blend. This we could say is the “Big Daddy” of Ethiopian cuisine. With a deep red paprika colour, berbere is a blend of many spices with its base very much set in the red chilli corner.

It is often made at home in Ethiopia and thus everyone makes it their own style and of course see theirs as the supreme version. The process is a lengthy one, starting off with the large red chilli (Also called Berbere by the way) being dried and then crushed. Then a combination of onion, garlic, ginger, fenugreek, black cardamon, cumin, nutmeg and even cinnamon are added and the complete mixture is then ground to a fine powder. Of course “Mums” version is always the best.

Berbere is usually made with fresh onion, garlic and ginger, but you can of course use dried powders, although not the same. But give it a go and have fun. If you want the real deal, we would suggest that you buy some, preferably direct from a source in Ethiopia. A few notes on herbs & spices in Ethiopian Berbere. Cumin. This is not the same as regular cumin you get in stores outside of Ethiopia. In fact it is nothing like it and has no features in look, smell or taste. ጥቁር አዝሙድ or Tikur Azmud. In English it is commonly referred to as Black Cumin or Black Caraway, although it has no relation to the common Cumin or Caraway that is used as a spice in cooking. It is also known as Black Seed (Nigella Sativa). Black Cardamon. Again these are very different from the Indian types found outside of Ethiopia. They are much much bigger and contain, many small seeds that have a eucalyptus aroma. Korerima or Korarima (Aframomum corrorima) are a vital part of Ethiopian cooking and although you can find the smaller black cardamon that are sometimes use in Indian cooking, they do not contain the same punch. Using green cardamon will result in a 100% failure in your berbere, these are so different, there is is just no point trying them. So the bottom line is, Ethiopian Berbere is fairly hard to make properly, even if you have all the correct ingredients. Now do not let this stop you having a go and creating your own, but if you need that authentic Ethiopian, it will take a lot of practice and as we have found, Mums version beats ours overtime. You can find many Recipes on our site on both the Recipes Pages and the Video Section. Please let us know how you got on!

በርበሬ

ይህን የኢትዮጵያ የምግብ አዘገጃጀት ዋና የሆነውን ሳይጠቀሙ በማብሰል ብቃትዎ ለመዝለቅ አይችሉም። ይህን ቅመም የኢትዮጵያ ምግብ “ትልቁ አባት” ብለን ልንሰይመው እንችላለን። ባለ ጥልቅ ቀይ ቀለሙ በርበሬ የተለያዩ አይነት ቅመሞች ውጤት ቢሆንም ዋነኛ መሰረቱ ዛላ በርበሬ ነው

አብዛኛውን ጊዜ በተለምዶ ቤት ውስጥ የሚሰራና እያንዳንዱ የራሱ በሆነ ዜዴ የሚያዘጋጀው ስለሆነ ሁሉም የየራሱን ከሁሉም የበለጠ እንደሆነ ያምናሉ:: ሂደቱም ጊዜ የሚወስድ ነው ፣ የሚጀምረው ከትልቁ ቀይ ቃሪያ (በነገራችን ላይ ዛላ በርበሬ ይባላል) ከደረቀ በኋላ ይከሰከሳል:: በመቀጠልም ከሽንኩርት ፣ ከነጭ ሽንኩርት ፣ ከዝንጅብል ፣ አብሽ፣ ኮረሪማ ፣ ጥቁር አዝሙድ ፣ ከሙን ፣ ቆንዶ በርበሬ እና ቀረፋ ሳይቀር ከተዋሀደ በኋላ የተሟላው ድብልቅ ጥሩ ሆኖ ይፈጫል:: አወ ልክ ነው “የእናቶች” የሙያ ውጤት ሁልጊዜ አሪፍ ነው::

በተለምዶ በርበሬ የሚዘጋጀው ከአዲስ ሽንኩርት ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ዝንጅብል ነው ፣ ነገር ግን እንዳስፈለጊነቱ በደረቅ ዱቄት መልክ መጠቀም ይቻላል:: ምንም እንኳ ተመሳሳይ ባይሆንም:: ነገር ግን ይሞክሩት እና ይደሰቱ:: እውነተኛውን ነገር ከፈለጉ ግን ፣ በቀጥታ እንድትገዙ እንመክራለን ፣ ማለትም ቀጥታ ከኢትዮጵያ ምርቶች:: የተወሰኑ ማስተዋሻወች በ ኢትዮጵያ ቅጠላ ቅጠል እና የበርበሬ ቅመሞች:: ከሙን፦ ይህ ከሙን ከኢትዮጵያ ውጭ ካሉ ሱቆች እንደምታገኟቸው ሌኮች ከሙኖች አይደለም:: በርግጥ እንደውም በሽታም ሆነ በጣዕሙ እንዲሁም በይዘቱ ምንም የሚያመሳስል ነገር የላቸውም::

ጥቁር አዝሙድ፦ በእንግሊዘኛው የተለመደው አጠራር ብላክ ከሙን ወይም ብላክ ካራዋይ ነው ፣ ምንም እንኳ ለማብሰል ከተለመደው ከሙን ወይም ካራዋይ ቅመም ጋር ግንኙነት የለውም:: ጥቁር ዘር(ኒጌላ ሳቲቫ) በመባልም ይታወቃል:: ብላክ ካርዳሙን፣ ይህም ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኘው የህንድ አይነቱ የተለየ ነው

እነዚህኞቹ በጣም በጣም ትልቅና በውስጣቸው ብዙ ትንንሽ ዘሮችን የሚይዙ ልክ እንደ ኢካላፕተስ ዛፍ ሽታቸው ያማረ ነው:: ኮረሪማ (አፍራሞሙም ኮሮሪማ) በኢትቶጵያ የምግብ አዘገጃጀት ውስጥ በጣም ጠቃሚው ነው እና ቢሆንም አንዳንዴ በህንዳዊያን የምግብ አዘገጃጀት እንደሚጠቀሙት ትንንሽ ኮረሪማወችን ልታገኙ ትችላላችሁ ያን ያህል ግን ቃና የላቸውም:: ለበርበሬ አዘገጃጀት አረንጓዴ ኮረሪማ መጠቀም 100% ስህተት ነው፣ ይህ በጣም የተለየነው፣ እንደዛ መሞከር ትርጉም የለሽ ልፋት ነው::

ስለዚህ ሊሰመርበት የሚገባው ነገር፣ ትክክለኛ ቅመም ቢኖርም እንኳ የኢትዮጵያን በርበሬ በአግባቡ ለማዘጋጀት ትንሽ አስቸጋሪ ነው:: ይህ ማለት ግን የራሳችሁን ሙከራ አታድርጉ ማለት አይደለም፣ ግን ጥሩ የሆነ ኢትዮጵያዊ ከፈለጋችሁ፣ እንደገኘነው ብዙ ልምምድ የሚያስፈልገው ነው፣ የእናቶች ልዩ አይነት ስራ የኛን በጊዜ ሂደት ይበልጠዋል:: በድረገጻችን በ ምግብ አዘገጃጀት መምሪያ ገጽ እና በቪዲዮ ክፍሎች የተለያዩ የምግብ አዘገጃጀት መምሪያ ታገኛላችሁ:: እንዴት እንዳገኛችሁት እባካችሁ አስታውቁን

No comments:

Post a Comment

Quick Guide to Every Herb and Spice in the Kitchen – በማድቤት ውስጥ የእያንንዱ ቅጠል እና ቅመም ፈጣን መመርያ

ደረቅ ቅጠሎች እና ቅመሞች አሳፎቲዳ (አሳፌቲዳ) – አሳፎቲዳ በህንድ አመጋገብ ውስጥ የምግብ መፈጨትን ለመርዳት የሚጠቅም ሲሆን የበሰለ ዝንጅብል ሽንኩርት ቃና ያለው ጠንካራ ሽታ አለው፡፡ አቾቴ ማጣበቂያ እና ዱቄት ...