Wednesday, March 20, 2019

የፖለቲካ ሊቁ ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ Walta Tv ጋር ካደረጉት ውይይት የተወሰዱ አንኳር አንኳር ነጥቦች ባጭሩ

የፖለቲካ ሊቁ ክቡር አቶ ጌታቸው ረዳ Walta Tv ጋር ካደረጉት ውይይት የተወሰዱ አንኳር አንኳር ነጥቦች ባጭሩ
#የህወሓት የሳቅ የሌሎች የለቅሶ ዘመን አልነበረም አሁንም ሌሎች እየሳቁ የህወሓት የሚያለቅስበት ዘመን ኣይኖርም።
#ትናንት አገር ካላሸበርኩ ሲሉ የነበሩትና ዛሬ በይቅርታ ስም ገብተው የሚንፈላሰሱበት ጎዳና ሳይቀር የተገየባው በኢህአዴግ ዘመን ነው።
#ጠበንጃ ይዞ በመንጎራደድ የሚፈጠር የስራ ዕድል የለምና ለውጥ የፈለገ ለወጣቶች የሚሆን የስራ ዕድል ይፍጠሩ።
#ችግሮች ሊኖሩበት ይችላል ብለን ወስነን ራሳችን ይዘን ያስረከብነውን አረጎራው እያሉ የሚቀበለት ከሆነ ህጋዊነቱ እዛው አብቅቷል ማለት ነው።
#ታደሰና በረከት ሰዎችን ይቆጣሉ ተብለው ቢከሰሱ ሃጥያት ቢሆንም ምክንያቱ ይገባኝ ነበር በሙስና ሲታሰሩ ግን በዚሁ ምክንያት ይታሰሩ የተባሉት 60 ቢሆኑ ራሴን 58ኛ ብየ በሚቀጥለው ደረጃ ስለማስቀምጣቸው እኔና አብይ ጨቋኞችን አስወግደን ራሳችን ተረኛ ጨቋኞች እንሁን እንዳልን ነው የምቆጥረው።
#በዚህ ሳምንት የማቸንፍ ስላልመሰለኝ ምርጫው ይራዘም የሚባል ከሆነ ምርጫው ለህዝብ ሳይሆን ለፓርቲ ነው የተቀረፀው እንደማለት ነው።
#"ፓርቲ እንደ ተስካር ድንኳን ኣላፊ ኣግዳሚው ነፍስ ይማር እያሉ የሚገቡበት ሳይሆን መርሁ ላይ ተግባብተው የሚጣሐሩበት ድንኳን ነው።"https://scontent-arn2-1.xx.fbcdn.net/v/t1.0-9/

No comments:

Post a Comment

Quick Guide to Every Herb and Spice in the Kitchen – በማድቤት ውስጥ የእያንንዱ ቅጠል እና ቅመም ፈጣን መመርያ

ደረቅ ቅጠሎች እና ቅመሞች አሳፎቲዳ (አሳፌቲዳ) – አሳፎቲዳ በህንድ አመጋገብ ውስጥ የምግብ መፈጨትን ለመርዳት የሚጠቅም ሲሆን የበሰለ ዝንጅብል ሽንኩርት ቃና ያለው ጠንካራ ሽታ አለው፡፡ አቾቴ ማጣበቂያ እና ዱቄት ...