ትግራይ ከኢትዮጵያ የተገነጠለች እንደሆነ፤ ዘግይታ በተጋሩ የተፈበረከችው ኢትዮጵያ እጣ ፈንታዋን ሳስበው እጅግ በጣም ያስፈራኛል። ትግራይና ተጋሩ የሱሜሌ፤ የኦሮምያ፤ የደቡብ፤ የቤኒሻንጉል ጉምዝ፤ ጋምቤላ፤ የዓፋርና ሌሎችም ኢትዮጵያዊነት ያስቀጠሉ ተኣምረኛ ህዝቦች ናቸው።
ትግራይና ተጋሩ ከኢትዮጵያ የተለዩ እንደሆነ ሃገሪቱ የጠላ ቂጣ እጣ ፈንታ የምትሆንባት እድል ከፍተኛ ነው። ምክንያቱም የማር ቀፎ ካለንብ፤ የሞባይል ቀፎም ካለ ሲም ካርድ ዋጋ እንደሌላቸው ሁሉ፤ ኢትዮጵያም ካለ ትግራይና ተጋሩ በታሪኳም፤ በሰላሟም፤ በልማቷም፤ በኣንድነቷም፤ በኃያልነቷም፤በመልከኣ ምድራዊ ኣቀማመጧም፤ በሃይማነቷም ባዶ መሆኗ ግልጽ ሊሆን ይገባል።
ተጋሩ በኣምላካቸው ላይ ከኦሪት ጀምሮ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ ስለሌላቸው፤ ኣንድ የሆኑ እለት የጥበባቸው ና የሃይላቸው ጥነካሬ ከኤስራኤላውያን እጅግ የላቀ መሆኑን በሙሴ ጽላት ኣመጣጥ ጥበብ፤ የሰሯቸው የህንጻዎችና የስነጽሁፎች ቅርሶች፤ በገዟቸው ሰፊው የዓለማችን ክፍሎችና ባደረጓቸው ኣንጸባራቂ ጦርነቶች ማየት በቂ ምስክር ነው። ኣሁን እቺ ለተጋሩ ሆና የማታውቅ ውለታ ቢስ፤ ትግራይና ተጋሩ ግን ለዘላለም የሚሞቱላት ኢትዮጵያ የምትባለው ሀገር፤ ላለፉት 130 ዓመታት ስሟንና ኣቅሟን ካጠለሹትና ካዳሸቁት ዘረኛና ትምክህተኛ ነፍጠኞች ኣላቀው ወደ ቀድሞው ገናና ስሟ ለማስመለስ በግንባር ቀደም ቀን ተሌት እየታተሩ የሚገኙት ተወደደም ተጠላም እነዚህ ተኣምረኛ ትግራይና ተጋሩ ናቸው።
ትግራይ ለኢትዮጵያ ምንድናት???
ኢትዮጵያን ያለ ትግራይ ሳስባት “ግርማ ሞገሷ ጠፍቶ የተራቆተች ታሪክ አልባ ሀገር” መስላ ትታያለች፡፡ አቢሲኒያ (የኢትዮጵያ የመጀመርያ ስያሜ ) በአክሱም ዘመነ መንግስት ጊዜ በሰሜን ኢትዮጵያ አክሱምና አካባቢው ይኖሩ የነበሩ ( አሁን ትግራይ የምንላቸው ህዝቦች) መጠርያ ነው፡፡ ስለዚህ ገና ከስሟ ስንጀምር “ትግራይ ለኢትዮጵያ ምንድናት?” የሚለው ጥያቄ መልሱ አንድና አንድ ነው፡፡
ትግራይ = ኢትዮጵያ ማረጋገጫው ደግሞ አቢሲኒያ = ኢትዮጵያ! 4ነጥብ !!!
ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ “ግርማ ሞገሷ ጠፍቶ የተራቆተች ታሪክ አልባ ሀገር ናት!!!
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መንግስት የሚባለው ፅነሰ ሐሳብ የፈለቀው ከዘመነ አክሱም በፊት በዳማት (ደአማት) ሲሆን ኢትዮጵያ በአንጋፋነቷና በታሪክ ቁንጮነቷ ከዓለም ተወዳዳሪ ሆና ስሟ የምትጠራበት ደረጃ ላይ የደረሰችውም በአክሱም ዘመነ መንግስት ነው፡፡
(በሌላ ኣነጋገር መንግስት መመስረት ለተጋሩ የሳር ቤት መስራት ያክል ቀላል ነው!)
ትግራይ ዳግማዊት እየሩሳሌምና ዳግማዊት መካ! (ኣከሱምና ነጃሽ)፡ እስላም ክርስትያኑ ከመካ ና እየሩሳሌም ቀጥሎ ሀይማኖቱን ያገኘበት የዓለም ክፍል መሆኑ ነው ትግረይ! ሸዋዎች በ15ኛው መክዘ ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያምን (በነገራችን ላይ ከርቤ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ? ለኦሮሞዎች እንተወው። ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም የሚባለው ገዳም በ1446 አጼ ዘርአ ያዕቆብ የኦሮሞ ምርኮኞችን ያስርበትና እነሱን ከርቤ በማጠጣት ያሰቃይበት የነበረ የተራራ ወህኒ ቤት ነበር። ኣሁን ይህንን ስፍራ በማህበረ ቅዱሳን ፊታውራሪነት ዳግማዊት እየሩሳሌም ብለው ይጠሩታል፤ ኣማናዊቷን ሳባዊትና ኣከሱማዊት ዳግማዊት እየሩሳሌም ዘኣከሱም ጽዮንን ለማደብዘዝ ከፍተኛ ጥረት መሆኑን ነው።
ኢትዮጵያ በዓለም ታሪክ የራሷ የሆነ ታሪክ እንዲኖራት የሆነውም በግዕዝ ቋንቋ ነው። ትግርኛና ግእዝ ማለት ጠቢቡ ሰለሞንና ቀዳማዊ ሚኒሊክ ማለት ናቸው። እናም የግዕዝ ቦክር ልጅ እንጂ ዲቃላ ቋንቋ ኣይደለም!!!
እኛ ኢትዮጵያውያን ሓሳባችን የምንገልፀው በራሱ ከዚህ ክልል በመጣ የቋንቋ ግንድ ነው!!! የቤተ ክርስትያኖቻችን ልሳንም ግዕዝ ነው!!!
የኢትዮጵያ መገለጫ ስለሆነው የስነ ህንፃና ቅርፅ ጥበብ ውጤቶች የሆኑ የተጋሩ ቅርሶችን የሌለበት ታሪክ እንዴት የኢትዮጵያ ታሪክ ልንለው እንችላለን?
የአክሱም ሐወልቶች፤ የይሓ ግንብና የተለያዩ ውቅር አብያተ ክርስትያናት፤ሃይማኖታዊ በዓላት ያላካተተ የኢትዮጵያ ታሪክ ሳስበው... ፊት የሌለው ሰው ኣይታችሁ ታውቃላችሁ? እንዴት ይለያል?
ኢትዮጵያውንን አንድ ስላደረገው የዓድዋ ድል ታሪክ፤ ማይጨው፤ ዶግዓሊ፤ ጉንደትና ጉራዕ ድሎች የአፄ ዮሀንስ፤ ራስአሉላ አባ ነጋ እና ባሻይ አውዓሎም በሚመሩት የትግራይ ህዝብ ድል ነው፡፡ እዚህ ላይ ኣንባብያን ልብ ልትሉት የሚገባው በባዶ እግሩ የሚታወቀው የሚኒሊክ ጦር ኣድዋ የገባው፡ የዓድዋ ጦርነት ኣብቅቶ ጦርነቱ በዓጋመ ግሎ ማክዳ ፤ መይዳ ወልዋሎ ፤ ሶበያ፤እንትጮ እና ስንቃጣ ግንባር በሚካሄድበት ወቅት ነበር!!! (መፅሓፍ ኣይንተሓማመን እንቢታን)
የሚኒሊክ ጦር ኣድዋ ሲገባ የዓድዋ ጦርነት ከማብቃቱ በፊት ቢሆን ኖር የኣድዋ ድል ታሪክ ኣዲስ ኣበባ ቀርቶ ሮም ላይ በየዓመቱ ይከበር ነበር!!! ለምን? ሚኒሊክ ከድርቡሾች ጋር ተመሳጥሮ ኣጼ ዮሃንስን በራሱ ጦር ያስገደለበት ክፉት ከጣልያን ጀነራሎች ጋር በመሆን ኣሉላ ኣባነጋን ለመድገም ሲዶልት ነበርና ነው!!! (መፅሓፍ ኣይንተሓማመን እንቢታ ኣንጻር ወረርትን፤መጣጥፍ ወዲ ደባስን ኣንብቡ)
ስለዚህ ከጅምሩ የሚኒሊክ ጦር ኣድዋ ሲገባ ጣልያንን ሊያግዝ እንጂ ሊዋጋ ኣልነበረም ኣመጣጡ! ኣሉላ ኣባነጋ እና ባሻይ አውዓሎም(በነገራችን ላይ ተኣምረኛው ባሻይ አውዓሎም የጣልያንን ብቻ ሳይሆን የሚኒሊክ ጓዳም በኣንክሮ ይሰልሉ ነበር) ይህን የጣልያንና የሚኒሊክ ሴራ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ የዓድዋ ጦርነቱ ሚኒሊክን ሳያስፈቅዱ ቀድመው ነበር የጀመሩት!! ለዚህም ነው የሚኒሊክ ጦር ኣግኣዝያን ምድር የዓድዋ ጦርነት ካበቃ ከ2 ሳምንታት በኋላ ዘግይቶ የደረሰው። እናም ተጋሩ ለኢትዮጵያ ተወደደም ተጠላም እስትንፋሷ ናቸው።
ንግስተ ሳባ፤ ቀዳማዊ ምኒልክ፤ ቅዱስ ያሬድ፤ ፈላስፋው ዘረዓ ያእቆብ (ወዲ ሽረ)፤ ኢዛና፤ አብርሀ ወ አፅብሃ፤ አፄ ካሌብ፤ አፄ ዮሀንስ፤ራስአሉላ አባ ነጋ፤ ባሻይ አውዓሎም፤ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ የሌሉበት ኢትዮጵያዊ ታሪክና ኢትዮጵያ ምን ትርጉም ኣለው???
አይደለም ትግራይ ብትነጥሉ ከትግራይ የሆነ አካል ብትቀንሱ ራሱ የኢትዮጵያ ታሪክ ይጎድላል!!!
· አክሱምን ብትቀንሱ ቅዱስ ያሬድን የሚያክል ሊቅ ከአክሱም ፅዮንና ከአክሱም ሐወልት ጋር ማጣት ነው፡፡
· ዓድዋን ብትነጥሉ በተጋሩ ፊታውራሪነት የተገኘው የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነውን የታሪክ መዕከል ማጣት ነው፡፡
· ሽረን ብትቀንሱ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ዘርዐ ያእቆብን ማጣት ነው፡፡
· ተምቤንን ብትነጥሉ አፄ ዮሀንስና ራስ አሉላ አባነጋን የመሰሉ ኢትዮጵያዊና አፈሪካዊ ጀግኖችን ማጣት ነው፡፡
· ዓጋመን ብትቀንሱ የእስልምና እምነት ምንጭ አልነጃሺን ማጣት ነው፡፡
ብቻ ኢትዮጵያ ያለ ትግራይ . . . ዓሣ ያለ ባህር ብንለው በደንብ ይገልጸዋል!!! ስለዚህ፦ ትግራይ = አቢሲኒያ፥ አቢሲኒያ=ኢትዮጵያ
· Simpy Ethiopia is made in Tigrai by Tegaru for Others.
እናም ትግራዋይነት ተገልጦ የማያልቅ የተኣምር መጽሃፍ ነው!!! የትግራይን ህዝብ ኣክብሮና ተንከባክቦ መያዝ ማለት የኢትዮጵያን ህልውና ማስቀጠል መሆኑን ኣምኖ መቀበል ለምርጫ የማይገባ ሃቅ ነው። ባጭሩ ተጋሩ የኢትዯጵያ የታሪክ፥ የሃይማት እና የፖለቲካ ቋት ብቻ ሳይሆኑ እስትንፋስም ናቸው፡፡ ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን የኢትዮጵያን ህልውናን ኣደጋ ላይ መጣል ማለት ነው።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Quick Guide to Every Herb and Spice in the Kitchen – በማድቤት ውስጥ የእያንንዱ ቅጠል እና ቅመም ፈጣን መመርያ
ደረቅ ቅጠሎች እና ቅመሞች አሳፎቲዳ (አሳፌቲዳ) – አሳፎቲዳ በህንድ አመጋገብ ውስጥ የምግብ መፈጨትን ለመርዳት የሚጠቅም ሲሆን የበሰለ ዝንጅብል ሽንኩርት ቃና ያለው ጠንካራ ሽታ አለው፡፡ አቾቴ ማጣበቂያ እና ዱቄት ...
-
Jump to navigation Jump to search Tigrayans ተጋሩ Total population c. 9-11 million' Regions with significant populations ...
-
ከዮሴፋዊ ዕጣ ፋንታ ወደ ቃየናዊ ዕይታ ከያዕቆብ ልጆች መካከል፤ አንዱ ዮሴፍ የሚባል ነበር፡፡ ዮሴፍ፤ ወላጆቹ ያከብራል፤ ይወዳልም፡፡ የልጅ ግዴታውም ይወጣል፡፡ ዮሴፍ ለወንድሞቹም፤ ወንድማዊ ፍቅሩ ይለግስላቸዋል፡፡...
No comments:
Post a Comment